የእግዚአብሔርን ተልዕኮ በማካፈል የሚገኝ ደስታ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2020

ከሐምሌ 11 - ሐምሌ 17

4ኛ ትምህርት

Jul 18 - Jul 24
የፀሎት ሀይል ለሌሎች መማለድሰንበት ከሰዓት

የሚከተሉትን ጥቅሶች ለዚህ ሳምንት ጥናት አንብቡ፡- ራዕይ 12፤7-9፤ ኤፌ 6፡12፤ ዕብ 7፡25፤ ኤፌ 1፡15-21፤ ዳን 10፡10-14፤ 1ዮሐ 5፡14-16።


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በስራዋ እጅግ ሀይል ታደርጋለች።” (ያዕ 5፡16)

የ አዲስ ኪዳንዋ ቤተክርስቲያን አባላት ፀሎት እንደሚያስፈልጋቸው ተሰምቷቸዋል። “ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።” (ሓዋ. 4፡31)። ደቀ መዛሙርቱ እንደፀለዩ ልብ በሉ። በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው የእግዚአብሄርን ቃል በድፍረትና በመተማመን ተናገሩ። በፀሎታቸው በመንፈስ ቅዱስ መሞላታቸው እና የእግዚአብሔርን ቃል በማወጃቸው መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለ። “ደቀ መዛሙርት ስለራሳቸው መባረክ ብቻ አልነበረም የጠየቁት። የነፍሳት ድነት ሸክም ተሰምቷቸው ነበር። ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ መዳረስ እንዳለበት ስላወቁ ክርስቶስ ቃል የገባላቸውን ሀይል ጠየቁ `Ellen G. White, The Acts of the Apostles, p.37::

እግዚአብሔርን ስንፈልግ እና ለሌሎች እየማለድን ስንጸልይ እግዚአብሔር ሌሎችን ወደ እርሱ እንድንመልስ እና ወደ መንግስቱ ለመጥራት እንድንደርሳቸው መለኮታዊ ጥበብ እንዲሰጠን በልቦናችን ውስጥ ይሰራል(ያዕ 1፡5)፡ እኛ ሙሉ በሙሉ ልናስተውል በማንችለው ሁኔታ በሃይል በህይወታቸው ሊሰራና ሊስባቸው ይችላል (1ዮሐ.5፡14-17)። የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለሐምሌ 18 ሰንበት ይዘጋጁ።

ሐምሌ 12
Jul 19

2 ትዕይንተ አለማዊ ተጋድሎ


ራዕይ 12፡7-9፤ ኤፌ 6፤12 እና 2ቆሮ 10፡4ን አነፃፅሩ። እነዚህ ጥቅሶች ለሌሎች በምንጸልየው የምልጃ ፀሎት መረዳታችን ላይ ተፅዕኖን የሚፈጥሩብን እንዴት ነው?መጽሐፍ ቅዱስ በሚታየውና በማይታየው አለም ውስጥ ያለውን ነገር ግልጥ አድርጎ ይነግረናል። በመልካም እና በክፉ፣ በጽድቅ ሀይላትና በጨለማ ሀይላት፣ በክርስቶስና በሰይጣን መካከል ተጋድሎ አለ። በዚህ ትዕይንት አለም ግጭት ውስጥ እግዚአብሔር የሰዎችን ነፃነት ያከብራል። ፈቃዳችንን ፈፅሞ አይቆጣጠርም ወይንም ህሊናችንን አያስገድድም። መንፈስ ቅዱስን የላከው ወንድና ሴት ልጆች ወደ መለኮታዊ እውነት እንዲመጡ ለመውቀስ ነው (ዮሐ 16፡7-8)። ሰማያዊ መላእክት ወደ ፍልሚያው በመግባት ሰዎች ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲገቡ ተፅዕኖ ያደርጋሉ (ዕብ.1፡14)። እግዚአብሔር ራሱ ወደራሱ እንዲመጡ ለማድረግ በሰዎች ህይወት ውስጥ መልካም የሆኑ አጋጣሚዎችንና ክስተቶችን ያዘጋጃል።

እግዚአብሔር የማያደርገው የእኛን አዕምሮ ማስገደድ ነው። ማስገደድ የእግዚአብሔር መንገድ ተቃራኒ ነው። ማስገደዱ የተዋሀደው በፍቅር መርህ ሲሆን ይህ ደግሞ የአገዛዙ መሠረት ነው። እዚህ ጋር ነው እንግዲህ ፀሎት አስፈላጊ የሆነው። እኛ ከመፀለያችን አስቀድሞ እግዚአብሔር ሰዎችን ለመድረስ ማንኛውንም ነገር እያደረገ ቢሆንም ፀሎታችን የሀያሉ አምላክ ሀይል እንዲገለጥ ያደርጋል። ለሌሎች ስንፀልይ ሳለ የኛን የመምረጥ ነፃነት ያከብራል ካለመፀለያችን ይልቅ ስንጸልይ በመልካም እና ክፉ መካከል ካለው ተጋድሎ የበለጠ ነገርም ማድረግ ይቻለዋል።

ይህን አባባል በደንብ አስተውሉ በመልካምና በክፉ መካከል ባለው ተጋድሎ ውስጥ ፀሎት ልዩነትን ያመጣል። ክርስቶስን ስለሚያውቁ ሰዎች ስንፀልይ መለኮታዊ በረከት ወደ ህይወታቸው እንዲፈስ የሚያደርገው መስመር ይከፈታል። እግዚአብሔር ለነርሱ ለመፀለይ የምናደርገውን ምርጫ ያከብራል በሚፀልዩ ሰዎች ስምም ሃያል ሥራን ያደርጋል። ለሌሎች ስለመማለድ የጸሎት ርዕስ ስናነሳ የእግዚአብሔርን ሥራ ሙሉ በሙሉ መረዳት እንደማንችል በትህትና ልብ ልንገነዘብ ያስፈልገናል። ነገር ግን ለራሳችንና ለሌሎች በቀጣይነት እንዳንጸልይና ፀሎት በረከትን እንዳናገኝ ሊያግደን አይገባም። ፀሎትን ችላ ከማለት ይልቅ በምንፀልይበት ጊዜ እግዚአብሔር በሃይል የሚሰራው ለምንድነው ጉዳዩ እንዴት እንደሚከናወን ሙሉ በሙሉ ባናስተውልም መጽሀፍ ቅዱስ ለሌሎች እንድንጸልይ ብቻ የገፋፋን ለምን ይመስላችኋል?

ሐምሌ 13
Jul 20

3 የሱስ፡ ለሌሎች የማለደው ሀያል


ሉቃስ 3፡21፣ ሉቃስ 5፡16 እና ሉቃስ 9፡18ን አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች የየሱስ የፀሎት ህይወት ውጤታማ ከሆነው አገልግሎቱ ጋር ስላለው ተዛምዶ ምን ያስተምረናል?የየሱስ ህይወት ከአባቱ ጋር በቀጣይነት መለኮታዊ የሆነ ህብረትን በማድረግ የተገለፀ ነው። በተጠመቀ ጊዜ መሲሃዊ አገልግሎትን ከፈተና ሰማያዊ አላማው እንዲፈፀም ለመለኮት ሀይል ጸለየ። መንፈስ ቅዱስ የአባቱ ፈቃድ እንዲከናወን እና ከፊት ለፊቱ ያለውን ስራ እንዲፈጽም ሃይልን ሰጠው። አምስት ሺህ ሰዎችን መመገብም ሆነ፣ የለምጻሞቹ መፈወስ አልያም ከአጋንንት ነፃ ማውጣት በመልካምና በክፉ መካከል ያለው ፍልሚያ የሲኦልን ሃይል ማፈራረሻ ሀይለኛ መሳሪያው ፀሎት መሆኑን የሱስ አውቋል። ፀሎት የኛን ረዳት አልባነት እና ደካማነት ከእግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት ጋር የሚያስተሳስር ሰማያዊ ቅባት ያለበት ዘዴ ነው። ወደርሱ ስንፀልይ የሌሎችን ልብ ሊነካ ወደሚቻለው ብቸኛ አምላክ ራሳችንን ከፍ የማድረግ መንገድ ነው።

ሉቃስ 22፡31-34 እና ዕብ.7፡25ን አንብቡ። የሱስ ጴጥሮስ ወደፊት ለሚገጥመው ፈተና እንዲዘጋጅ የሰጠው ዋስትና ምን ነበር? እያንዳንዳችን ፈተና ሲገጥመን ዋስትና እንዲሆነን የሰጠን ነገርስ ምንድነው?ነፍሳትን ውጤታማ በሆነ መንገድ የማረኩ ሰዎች የፀሎት ሰዎች ናቸው። የሱስ የጴጥሮስን ስም ጠርቶ ፀልዮአል። ከባድ ፈተና ጴጥሮስን ባጋጠመው ጊዜ ለእርሱ እንደሚፀልይለት አረጋገጠለት ሰይጣን ጴጥሮስ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋፋት ያለውን እምቅ ሀይል ጠንቅቆ ተረድቷል። ጴጥሮስ በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላይ ያለውን አዎንታዊ ተፅዕኖ ለማፍረስ የተቻለውን ነገር ሁሉ ለማድረግ አቀደ። በነዚህ ፈተናዎች ጊዜ ሁሉ ግን የሱስ ለጴጥሮስ ይፀልይ ነበር።

የጌታም ፀሎት ተሰምቷል። አዳኙ ለኛም እንደሚፀልይ ማወቃችን ምን ያክል አስደናቂ እውነታ ነው። ለሌሎች በመማለድ የመፀለይ ተግባር ላይ እንድንሳተፍ እና ሌሎችን በስም እየጠራን በዙፋኑ ፊት ከፍ አድርገን እንድናቀርብ ይጋብዘናል። በፀሎት መፅናታችን ለምንፀልይላቸው ሰዎች ለመድረስ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ እንደምንደገፍ እውቅናን ይሰጥልናል። አሁን ስለማን እየፀለያችሁ ነው? ነገሮች ምንም ያክል አስቸጋሪ ሆነው ቢታዩም ተስፋ ያለመቁረጥ አስፈላጊነት ምን ያክል ነው?

ሐምሌ 14
Jul 21

4 የጳውሎስ የምልጃ ፀሎት


ለሌሎች የምልጃ ጸሎትን ማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። በአገልግሎቱ ወቅት በሙሉ ጳውሎስ እርሱ በወንጌል እንቅስቃሴ ምክንያት ባቋቋማቸው ቤተክርስቲያን ስለነበሩ አዲስ ስለተለወጡ ሰዎች ጸልዮአል። ጳውሎስ ሲፀልይ አንድ ነገር እንደሚሆን እና ካልፀለየ ምንም እንደማይሆን ያምናል። ምንም እንኳ ከሚወዳቸው ወገኖቹ ቢለይም አንዳቸው ላንዳቸው ሲጸልዩ በልቦናቸው አንድ ሆነው እንደሚተሳሰሩ ተረድቷል።

ኤፌ.1፡15-21ን አንብቡ። ከዚህ በታች ባለው ባዶ መስመር ጳውሎስ ስለ ኤፌሶን ሰዎች የጠየቃቸውን ጥያቄች ዘርዝራችሁ ፃፉ። እግዘአብሔር በተለየ ሁኔታ እንዲሰጣቸው የጠየቀው ነገር ምንድነው?ጳውሎስ ለኤፌሶን አማኞች የፀለየው ፀሎት አስደናቂ ነው። በመለኮታዊ እውነት ልቦናቸው አብርቶ የዘላለም ሕይወት ተስፋ ይሰጣቸው ዘንድ እግዘአብሔር ጥበብና መንፈሳዊ መገለጥ እንዲሰጣቸው ፀለየ። በህይወታቸው ታላቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን የሃይል ሥራ እንዲያጣጥሙ ፀለየ። ይህ አምላክ እጅግ ሃያል እና ታላቅ የሱስን ከሞት ያስነሳው፤ በእርሱም የዘላለም ሕይወት ተስፋን የመሰረተ ነው። ፀሎቱን የደመደመው “በክርስቶስ ክብር ሙላቱ” እና “እርሱ እንደሚወርስ” በመናገር ነው። የኤፌሶን ክርስቲያኖች ጳውሎስ እንደሚፀልይላቸው እና ስለምን እንደሚፀልይላቸው በማወቃቸው መደፋፈር ሞላባቸው።

ፊሊ.1፡3-11ን አንብቡ እና የጳውሎስን የፀሎት ድምጸት አስተውሉ። የፊሊጵስዩስ ቤተክርስቲያን አባል ብትሆኑና ጳውሎስ ለእናንተ እንደሚፀልይና ስለ ፀሎቱ ደግሞ ገልፆ የላከውን ደብዳቤውን ብትቀበሉ ምን ይሰማችኋል? በቃላቱ ውስጥ ምን የተስፋ ቃላትስ ይገኛሉ? በተመሳሳይ ጊዜ ምን የግሳጼ ቃላትንስ አሉት?በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ቃላት በተስፋ ቃላት የተሞሉ፣ እግዚአብሔር በእርሱ ዘንድ የሚመኝልን ምኞት የሚገለጥልን የሱስን በማወቅ በፍቅርና በእውቀት ሙላት እንዲሆን ይጠራናል።

ሐምሌ 15
Jul 22

5 የማይታየው ሀይል በስራ ላይ


የምልጃ ጸሎት “ታላቅ ተጋድሎ” ብለን በምንጠራው በመልካምና በክፉ መካከል ባለው ትግል ውስጥ ሃይለኛ መሣሪያችን ሆኖ የሚያገለግል ነው። ከነዚህ ተጋድሎዎች መካከል ግልጽ ሆኖ የተገለጠው አንድ ክፍል የሚገኘው በዳንኤል 10 ላይ ነው። እንደምታስታውሱት ነብዩ ኤርምያስ አይሁዶች ለሰባ አመታት በባቢሎናውያን የባርነት ቀንበር ስር እንደሚውድቁ ተንብዮ ነበር። በዳንኤል የህይወቱ መገባደጃ ላይ የአይሁዳውያን የምርኮ ጊዜ ትንቢት ማብቂያው ሆነ። ዳንኤል ስለዚህ ጉዳይ ያሳስበው ነበር። ስለ ኤርምያስ የትንቢት ቃል ፍፃሜ ማስረጃነት በመጠኑም ቢሆን ተረድቷል። ህዝቦቹ አሁንም በባርነት ስር ናቸው።

ባቢሎናውያን በሜዶና ፐርሺያ ቢሸነፉም አይሁዳውያን አሁንም በባርነት ቀንበር ስር ነበሩ። ዳንኤል ለሶስት ሳምንታት ጾመ ፀለየ። ለህዝቦቹ በነቃ ልብ እየማለደ ፀለየ። ከሦስት ሳምንታት ማብቂያ በኋላ በክብር የተሞላው መልአክ ታየው። ዳንኤል 10፡10-14ን አንብቡ። የዳንኤል ፀሎት የተሰማው መቼ ነበር በጊዜያዊነት ለፀሎት ጋሬጣ የሆነበት ነገር ምን ነበር?ይህ አስደማሚ ክፍል ነው። ሙሉ በሙሉ ማስተዋል እንድንችል አንዳንድ ገጸ ባህርያትን ለይተን እናውጣ። የፋርስ መንግስት አለቃ ማነው? በእርግጠኝነት ሳይረስ አይደለም። እርሱ የፐርሺያ መንግስት ንጉስ ነው። “የፐርሺያ መንግስት አለቃ” የሚለው አገላለጽ የሚያዘነብለውና የሚወክለው ሰይጣንን ነው። የሱስም ሲጠራው “የዚህ አለም አለቃ” ወይንም “የዚህ አለም ገዢ” ይለዋል (ዮሐ. 12፡31፤ ዮሐ. 14፡30)።

ጳውሎስም “በአየር ላይ ስልጣን ያለው አለቃ” ብሎ ይሰይመዋል (ኤፌ.2፡2)። የፐርሺያ አለቃ ሰይጣንን ከወከለ፣ ሚካኤልስ ማነው ታዲያ? ሚካኤል የሚለውን ቃል መጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 5 ጊዜ ያህል ተጠቅሶ እናገኛለን (ራዕይ 12፡7፤ ይሁዳ 9፤ ዳን. 10፡13፣ 21 እና ዳን. 12፡1)። እነዚህን ጥቅሶች በጥንቃቄ ስናጠና ሚካኤልን (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማለት ነው) ከሰይጣን ጋር በነበረው ቀጥተኛ ውጊያ የመላዕክት ሁሉ አለቃ ስለሆነው የሱስ የሚገልፅ ሌላ ተለዋጭ ስም እንደሆነ ይነግሩናል። ክርስቶስ ዘላለማዊ፣ ቀድሞ የነበረ እና መለኮታዊ ሀይል ሁሉ የተሰጠው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። እንደ መላዕክት አለቃነቱ አንዱ ተግባር ሰይጣንን ማሸነፍ እና እስከዘላለሙ ማጥፋት ነው።

ዳንኤል 10 መጋረጃውን ገለል አድርጎ ይከፍተውና በመልካምና በክፉ መካከል ያለውን ተጋድሎ ይገልፅልናል። ዳንኤል እንደፀለየው ሀያል የሱስ የሆነው ሚካኤል የሲኦልን ሀይል ለመምታት ከሰማይ ወረደ። እኛ ልናየው ባንችልም የሱስ ለሌሎች የምንፀልየውን የምልጃ ፀሎት ለመመለስ በስራ ላይ ነው። እርሱ ሀያል አዳኝ ነው። አንዲትም ፀሎት ሳትታይ የምታልፍ አይደለችም። የታላቁ ተጋድሎ እውነታነት በህይወት ውስጥ ሲከናወን እንዴት ያዩታል? የዚህ ተጋድሎ እውነታ ምን አይነት ምርጫ እንድታደርጉ አደረጋችሁ?

ሐምሌ 16
Jul 23

6 የፀሎት ትኩረት


በመላው መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ በተለየ ነገር ላይ ትኩረት ያደረጉ ፀሎቶች አሉት። ፀሎት እንዲሁ በከንቱ ነፍሳትን የመናፈቅ ሁኔታ አይደለም። የተለየ የፀሎት ጥያቄን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነው። የሱስ በተለየ ሁኔታ ለደቀ መዛሙርቱ ፀለየ። ሐዋርያው ጳውሎስ በተለየ ሁኔታ ለኤፌሶን፣ ፊሊጵስዮስ እና ቆላስይስ ክርስቲያናት ፀለየ። ወጣት ለሆኑ የሥራ ባልደረባዎች ልክ እንደ ጢሞቲዎስ፣ ቲቶስ እና ዮሐንስ ማርቆስ ላሉት ፀለየ።

1ሳሙ. 12፡22-24 እና ኢዮብ 16፡21ን አንብቡ። እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ያላቸው ተመሳሳይ ሀሳብ ምንድነው? ስለ ምልጃ ፀሎት ምን የሚነገሩን ነገርስ አለ?ሳሙኤል እና ኢዮብ በንቃት፣ ከልብ ስለሚደረግ የተለየ የምልጃ ፀሎት አስፈላጊነት አፅንኦት ይሰጣሉ። ሳሙኤል እንዲህ ብሎ ጮኸ “ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ” (1ሳሙ 12፤23)። ኢዮብ በተናገረው ቃል ላይም ሳሙኤል የተናገረው ሃሳብ ተስተጋብቶ ይስተዋላል “የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ?” (ኢዮብ 16፡21)። ክርስቶስን ለማያውቁ ወንዶችና ሴቶች እግዚአብሔርን መጠየቅ ነው የኛ ተግባር።

1ዮሐ 5፡14-16ን አንብቡ። ለሌሎች ስንማልድ ምን ይከሰታል?ለሌሎች ስንጸልይ ለነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔር በረከት በእኛ በኩል እንዲተላለፍ መስመር ያደርገናል። የህይወት ውሃ ምንጭ ከሰማያዊ ዙፋን ፈሶ በኛ አልፎ ወደነርሱ ይደርሳል። የቅን ልቦች የምልጃ ጸሎት ድምጽ የሰይጣንን ጭፍሮች ያንቀጠቅጣቸዋል። “ሰይጣን ይህንን ተቀናቃኝ የሚሆንበትን ተማፅኖ ሊቋቋም አይቻለውም ምክንያቱም በሀያሉና ብርቱ ጌታ ፊት ይፈራል ይሸበርማል። ከልብ በሚለዩ ፀሎቶች ድምፅ መላው የሰይጣን ጭፍሮች ይሸበራሉ

`Testimonies for the church, vol. 1 p. 346:: ፀሎት የጠፉ ወንድ እና ሴት ነፍሳቶችን ለማግኘት በምናደርገው ትግል ውስጥ ከመለኮታዊ የሃይል ምንጭ ጋር እንድንገናኝ ያደርገናል። ማቴ. 18፡18-19ን አንብቡ። ከምልጃ ጸሎት ጋር ይህ ጥቅስ እንዴት ይገናኛል? ይህ ጥቅስ ጌታንስ ስላላወቁ ሰዎች ድነት እንድንፀልይ የሚያበረታታን እንዴት ነው?

ሐምሌ 17
Jul 24

7

ተጨማሪ ሐሳብ


Read Ellen G. White, `The Privledge of prayer,` pp. 93-104, in steps to chirst; `work for church members,` pp. 19-24, in Testimonies for the church vol. 7:: ለሌሎች ስንፀልይ እግዚአብሔር የሰዎችን ህይወት ለመለወጥ ሰማያዊ ሀብቶችን በሙሉ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለእርሱ ያለንን ክብር እና በእርሱ ሃይል ላይ ያለንን መመካት ያከብራል። ፀሎታችን ወደ ዙፋኑ ሲያርግ መላዕክት ትእዛዙን ለመፈፀም ይወጣሉ። “የሚያገለግሉ መላዕክታት በቅንነት እና ህያው እምነት ለመነጩ ፀሎቶች ምላሽ መስጠት የሚችለውን የየሱስን ክርስቶስን ምላሽ ከዙፋኑ ተቀብለው ወዲያው ለመታዘዝ ይጠባበቃሉ” - Ellen G. White, Selected messages, book 2, p. 377። ምንም ጸሎት ጠፍቶ እንደማይቀር እና ምንም ፀሎት በእግዚአብሔር ዘንድ እንደማይረሳ ማረጋገጫ አለን።

እርሱ በሚያውቀው ትክክለኛ ጊዜና ቦታ ላይ ለመመለስ በሰማይ ግምዣ ቤት ተጠብቀውልናል። “የእምነት ፀሎት ፈፅሞ አይጠፋም ነገር ግን እኛ ለጠበቅነው ለተለየ ነገር ምላሽ ለመቀበል ሁልጊዜ በድፍረት መጠየቃችን ነው።” Ellen G. white, Testimonies for the church, vol. 1, p. 231። ክርስቶስን ለማያውቁ የትዳር አጋሮቻችን፣ ወንድና ሴት ልጆቻችን፣ ዘመዶቻችን፣ ጓደኞቻችንና የሥራ አጋሮቻችን እንድንፀልይ ይህ ምን ማበረታቻ ይሰጠናል። አንዲትዋም እውነተኛ ፀሎት ጠፍታ አትቀርም። በምንጸልያቸው ፀሎቶች አፋጣኝ ምላሽን ሁልጊዜ ማግኘት ባንችልም እግዚአብሄር ግን ልቦችን እየቀሰቀሰ የሚገኝበት መንገድ አለው ይህን የምናስተውለው ደግሞ ዘላለማዊ ሕይወት ላይ ሆነን ነው።


የመወያያ ጥያቄዎች1.ፊሊ. 1፡19፤ቆላ.4፡2-3 እና 2ተሰ.3፡1-2ን አንብቡ። ጳውሎስ በእስር ቤት እያለ በፊሊጵስዮስ ሰዎች ፀሎት አማካኝነት ምን መተማመኛ አገኘ? የቆላስያስ እና የተሰሎንቄ ሰዎች በእርሱ ስም እንዲፀልዩ እንዴት ጠየቃቸው? እነዚህ የምልጃ ፀሎቶች ነፍሳትን ከመማረክ ጋር ያላቸው ተዛምዶ ምንድነው?

2.በታላቁ ተጋድሎ እውነታ ላይ ትኩረት አድርጉ፣ ከምንኖርባት አለም በስተጀርባ ያለውን ትርክት ፈጥሯል። ስለዚህ ተጋድሎ ያለው እውነት ስለ ፀሎት አስፈላጊነት እንድትረዱ የሚያግዛችሁ እንዴት ነው? አዎን፣ የሱስ ጦርነቱን አሸንፏል በእርሱ ጎራ ያሉ በስተመጨረሻ እንደሚያሸንፉ እናውቃለን። ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜም ስንፀልይ ለእርሱ ታማኝ የሚያደርጉንን ነገሮች በሙሉ ለማድረግ እንድንሻ እና ለሌሎች ድነት እንድንሰራ የመሆኑ አስፈላጊነት ምን ያክል ነው?

3.የምልጃ ፀሎትን በመጸለይ የበለጠ ውጤታማ ህይወት እንዳንኖር የሚያደርጉን አንዳንድ እንቅፋቶች ምንድናቸው? የእርሰዎ ፀሎት ለሚያሻቸው ላለመፀለለይ የሚያቀርቧቸው ሰበቦች(ካልዎት) ምንድናቸው?