የእግዚአብሔርን ተልዕኮ በማካፈል የሚገኝ ደስታ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2020

ከሐምሌ 4 - ሐምሌ 10

3ኛ ትምህርት

Jul 11 - Jul 17
በየሱስ አይን ሰዎችን መመልከትሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡- ማር.8፡22-26፤ ዮሐ.4፡ 3-34፤ ዮሐ. 1፡40-41፤ ማር.12፡28-34፤ ሉቃስ 23፡39-43፤ ሐዋ.8፡26-38።


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “እርሱም በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።” (ማቴ 4፤19)

የ ሱስ ነፍሳትን የሚማርክ ጌታ ነው። የሱስ በሰዎች መካከል የሚሰራበትን መንገድ በማየት በየሱስ ክርስቶስ በኩል ሌሎችን እንዴት ወደ ድነት እውቀት መምራት እንደምንችል እናወራለን። በህዝብ በተጨናነቁ የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አቧራማ የይሁዳ መንገዶች እና በሳር በተሸፈኑ የገሊላ ኮረብታዎች ላይ ከእርሱ ጋር ስንጓዝ ነፍሳትን ለማግኘት እርሱ የእግዚአብሔርን መንግስት መርሆዎች እንዴት እንደገለጠ እናስተውላለን።

የሱስ ወንዶች እና ሴቶች በሙሉ ለመንግስቱ ሊማረኩ እንደሚችሉ ተመለከተ። እያንዳንዱን ሰው ይመለከት የነበረው መለኮታዊ በሆነ የርህራሄ አይኑ ነበር። ጴጥሮስን ያየው የነበረው እንደ አስቸጋሪ እና አፉን ከፍቶ ጮክ ብሎ እንደሚናገር አሳ አጥማጅ ሳይሆን እንደ ሃያል የወንጌል ሰባኪ ነው። ያዕቆብ እና ዮሐንስን ይመለከት የነበረው ፈጥነው ግልፍተኛ እና ቁጡ እንደሆኑ ሳይሆን ፀጋውን በጋለ ስሜት እንደሚያውጁ ሰዎች ነው። በመቅደላዊት ማርያም፣ በሳምራዊትዋ ሴት እና ደም ሲፈሳት በነበረችው ሴት ልብ ውስጥ እውነተኛ የሆነ ፍቅርና ተቀባይነት የማግኘት ናፍቆት እንደነበራቸው ተመለከተ። ቶማስን እንደተጠራጣሪ ሳይሆን ትክክለኛ ጥያቄዎች እንዳለው ሰው ነበር ያየው። አይሁዳዊ ይሁን አሕዛብ፣ ወንድ ይሁን ሴት፣ በመስቀል ላይ የነበረው ወንበዴ ይሁን የመቶ አለቃው ወይንም በአጋንንት የተያዘው ሰው የሱስ ያየው እግዚአብሔር የሰጣቸውን አቅም እና በድነት መነፅር እይታ በኩል ነው።

የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለሐምሌ 11 ሰንበት ይዘጋጁ።

ሐምሌ 5
Jul 12

ሁለተኛ መነካት


በመጽሐፍ ቅዱሳችን ሙሉ የሱስ በሁለት ደረጃ የሰራው ብቸኛ ተኣምር አንድ ብቻ ነው። ይኸውም በቤተሳይዳ አካባቢ የተፈወሰው እውር ሰው ታሪክ ነው። ይህ ታሪክ ዛሬ ላይ ላለችው ቤተክርስቲያን ጊዜ ያልገደበውን ትምህርት ይሰጠናል። ይህ የሚያስተምረን ነገር ቢኖር እግዚአብሔር እያንዳንዱን አማኝ በመጠቀም ሌሎችን ወደየሱስ እንዲያመጡ ያለውን እቅድ ነው። “ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ” ዕውርም አመጡለት እንዲዳስሰውም ለመኑት።” (ማር.8፡22) እዚህ ጋ ያሉ ሁለት ወሳኝ ቃላት አሉ “አመጡለት” እና “ለመኑት” የሚሉ ናቸው። ይህ አይነ ስውር በራሱ ፍላጎት አልነበረም የመጣው፡፤ ወዳጆቹ ናቸው ፍላጎቱን አውቀው ወደርሱ ያመጡት፡፤ እርሱ ያን ያክል እምነት ላይኖረው ይችላል እነርሱ ግን ነበራቸው። የሱስ የዚህን ሰው እውርነት እንደሚፈወስ እምነት ነበራቸው።

በየሱስ የተደረጉና በአዲስ ኪዳን ውስጥ የታወቁ ወደ 25 የሚጠጉ የፈወስ ተአምራት አሉ። ከግማሽ በላዮቹ የሚሆኑት ዘመዶችና ጓደኞቸው ናቸው ሰዎቹን የሱስ እንዲፈውሳቸው ወደ እርሱ ያመጡት። እምነት ያላቸው ሰዎች ካልሆኑ በቀር ማንም ሰው እነዚህን ሰዎች ይዟቸው ሊመጣ አይችልም። የኛ ሚና “ማስተዋወቅ” እና ወደ የሱስ ማምጣት ነው። በማር.8፡22 ላይ ትኩረታችንን ያደረግንበት ሁለተኛው ቃል ለመኑት የሚለው ነው። “ተማጸኑት ጠየቁት ወይንም ደግሞ አጥብቀው ወተወቱ” ብለን ልንተረጉም እንችላለን። በጩኸትና በሁካታ ከታጀበ ተማጽዕኖ ይልቅ ዝግ ያለ፣ ርህራሄ ያለበት እና ጨዋነት የተሞላበት ተማጽኖን ነው የሚያሳየን። የዚህ ሰው ወዳጆች የሱስ ይህንን ሰው ለመርዳት መሻቱም ሀይሉም እንዳለው በማመን ነበር በርህራሄ የተማፀኑት። ይህ ሰው የሱስ መፈወስ እንደሚችል ላያምን ይችላል፣ ነገር ግን ወዳጆቹ ይህ እምነት ነበራቸው። አንዳንድ ጊዜ በኛ የእምነት ክንፎች ተሸክመን ሌሎችን ወደ ክርስቶስ ልናመጣ ይገባናል።

ማር.8፡22-26ን አንብቡ። የሱስ ሁለት ደረጃዎች አልፎ ይህንን እውር ሰው የፈወሰው ለምን ይመስላችኋል? ይህ ታሪከ ዛሬ ለየሱስ ልንመሰክር ላለን ሰዎች የሚያስተምረን ምን ነገር አለው?ሰዎችን በግልጽ አጥርተን የማናይበት እድል አለ አንዳንዴ ሰዎችን የምናየው ለእግዚአብሔር መንግሥት እጩዎች እንደሆኑ ሳይሆን ልክ “ዛፎቹ ሲራመዱ” አይነት ድንግዝግዝ ያለ ጭጋጋማነት ባለበት እይታ ይሆንን? ሰዎችን አጥርተን እንዳናይ የሚያደርገን ምን ነገር ያለ ይመስሎታል?

እግዚአብሔር ሰዎችን እንድንደርስ እንዴት እንደተጠቀመብን ከተማርንበት ግልጽ ከሆነ ትምህርት ባሻገር ከዚሀ ታሪክ ምን የምንማረው ነገር አለ? ህክምና እና መንፈሳዊነት ሁለቱም እንደ አብነት ሆነው የጠፉትን በመፈወስ እና ወንጌል በመስራት ትልቅ ሚና እንዳላቸው ይሄ ምን ያስተምረናል?

ሐምሌ 6
Jul 13

በተቀባይነት ውስጥ ያለ ትምህርት


እያንዳንዱን ሰው እንዴት በአዲስ መንገድ ማየት እንዳለባቸው ተምሳሌት ለመሆን የሱስ ደቀ መዛሙርቱ ሰዎችን በሰማያዊ አይን እንዲመለከቱ አስተማራቸው። እርሱ ሰዎችን የሚያይበት ሁኔታ አስደናቂ ነው። የሚያየው አሁን ያሉበትን ሁኔታ ሳይሆን ወደፊት ሊሆኑ የሚችሉትን ሁኔታ ነው። ሰዎች ጋር በተገናኘ ቁጥር ሰዎቹን ያከብራቸውና ስፍራ ይሰጣቸው ነበረ። እንደውም ብዙ ጊዜ ሰዎችን የሚይዝበት መንገድ ደቀ መዛሙርትን ያስደምማቸው ነበር። በተለይም ይህ እውነት ሆኖ የታየው ከሳምራዊትዋ ሴት ጋር በተገናኘበት ወቅት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን በቁፋሮ ጥናት የሚያጠኑ ሰዎች በአይሁድ እና ሳምራውያን መካከል ያለውን አስገራሚ ግንኙነት እንዲህ ተረድተዋል። በሳምራውያንና በአይሁዳውያን መካከል የነበረው ጥል ገና ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የጀመረ ነው። እንደ 2ነገ.17 መሰረት ሳምራውያን ከሜሶፖታሚያ ህዝቦች ዘር በ722 ከክርስቶስ ልደት በፊት የመጡና በአሶር ንጉስ አስገዳጅነት በሰሜናዊ እስራኤል እንዲሰፍሩ የተደረጉ ህዝቦች ናቸው። የያህዌን አምልኮ ከጣኦት የአምልኮ ተግባር ጋር ቀላቀሉ። “Archeological study Bible (Zondervan publishing, 2005). P. 1727 ከዚህ የጣኦት አምልኮ በተጨማሪ ተቀናቃኝ የሆኑ ቀሳውስትንና ቤተ መቅደስን በገሪዚም ተራራ ላይ መሰረቱ። ይህንን የስነ መለኮት አስተሳሰብ ልዩነትን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የሱስ ወደ ገሊላ ለመሄድ በሰማርያ ለማለፍ መምረጡ ግራ አጋብቷቸዋል።

የሱስ ሃይማኖታዊ ክርክር ለማድረግ ራሱን ወደዚህ ስፍራ እንዳላመጣ በማሰብ ተደንቀዋል። ይህቺ ሳምራዊት ሴት ለነበራት ተቀባይነት የማግኘት፣ የፍቅር እና የይቅርታ ናፍቆት በቀጥታ ደረሰላት። ዮሐ.4፡3-34ን አንብቡ። የሱስ ሳምራዊትዋን ሴት የቀረበው እንዴት ነበር? ክርስቶስ ላናገራት ንግግር የዚህች ሴት ምላሽ ምን ነበር? ለዚህ ክስተት ደቀ መዛሙርቱ የሰጡት ምላሽ ምን ነበር? የሱስስ እይታቸው እንዲሰፋ እንዴት አደረገ?የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እና ለእያንዳንዳችን ሊያስተምረን የሚናፍቀው ዘላለማዊ ትምህርት በቀላሉ ሲቀመጥ “የክርስቶስ መንፈስ ያለባቸው ሰዎች ሌሎችን የሚያዩት መለኮታዊ በሆነ የርህራሄ አይን ነው” Ellen G. white, The signs of the times, June 20, 1892

በእናንተ ባህል ወይም ማህበረሰብ ተጽዕኖ ምክንያት በንቀት እና በማንቋሸሽ የምታዩዋቸው ሰዎች እነማናቸው? አመለካከትዎን መቀየር የሚገባዎ ለምንድነው? ይህስ ለውጥን እንዴት ያመጣል?

ሐምሌ 7
Jul 14

ካሉበት ስፍራ መጀመር


አንድ ሰው ይህን ትክክለኛ አባባል ተናግሯል “በህይወት ውስጥ የምንጀምርበት ብቸኛ ስፍራ ያለንበት ቦታ ነው፤ ሌላ የምንጀምርበት ስፍራ የለንምና”። የሱስ ይህንን መርህ አጽንኦት ሰጥቶ ሐዋ.1፡8 ላይ ተናገረ “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ሀይልን ትቀበላላችሁ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”

የሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው መልእክት ለመረዳት የማይከብድ ግልጽ መልዕክት ነው፡- ካላችሁበት ጀምሩ። እግዚአብሔር ከተከላችሁ ስፍራ ላይ መስክሩ። በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ለመመስከር የተሻለ ዕድል ይመጣል እያልን ከማለም ይልቅ ይሄ የተሻለ ነው። ከእናንተ ጋር በጣም ቅርብ የሆነውን እድል በመለኮታዊ አይን ይመልከቱ።

በአለም ውስጥ በጣም የተማርን፣ አንደበተ ርቱዕ እና ባለ ተሰጥኦ መሆን አያሻንም። እነዚህ ባለ ተሰጥኦዎች ግን በአግባቡ ጥቅም እንዲሰጡ እገዛ እናድርግ በስተመጨረሻ የሚያስፈልጋችሁ እግዚአብሔርን መውደዳችሁ እና ለነፍሳት ያላችሁ ፍቅር ነው። ለመመስከር ፈቃደኛ እስከሆናችሁ ድረስ እግዚአብሔር ይህን እንድታደርጉ መንገድን ይከፍትላችኋል። ዮሐ.1፡40-41፤ ዮሐ.6፡5-11 እና ዮሐ.12፡20-26ን አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች እንድርያስ ስለነበረው መንፈሳዊ እይታ እና ለምስክርነት የተጠቀመበት አቀራረብ እንዴት እንደሆነ ምን ያስተምረናል?የእንድርያስ የህይወት ልምምድ የሚያስተምርን ታላቅ የሆነ ነገር አለው። ከራሱ ቤተሰቦች ነበር የጀመረው። በመጀመሪያ ስለ ክርስቶስ የመሰከረው ለወንድሙ ለጴጥሮስ ነው። ከዛ ታናሽ ብላቴና ጋር ልባዊ ግንኙነት ከመሰረተ በኋላ የሱስ ያን ተአምር እንዲፈፅም ምግቡን ሰጠው። እንድርያስ ለግሪካውያን ምን ማድረግ እንደሚገባው ያውቃል። ስለ ስነ መለኮታዊ ጉዳይ ከመከራከር ይልቅ ፍላጎታቸውን ተረድቶ ከየሱስ ጋር አስተዋወቃቸው።

ውጤታማ በሆነ መንገድ ነፍሳትን የመማረክ ጥበብ ከሌሎች ጋር ቀና የሆነ እንክብካቤ ያለበትን ግንኙነት የመመስረት ጥበብ ነው። በጣም የቅርብዎ የሆኑ የሱስን ግን ስላላወቁ ሰዎች እስቲ አስቡ። እናንተ ህይወት ውስጥ ሩህሩህነትንና ለሰዎች ግድ እንደሚላችሁ ይገነዘባሉን? ህይወትዎ ለወንጌል ማስታወቂያ የሆነ ህይወት ነው? ለእግዚአብሔር ወዳጆችን የምናፈራው የሱስን በመመስከር ነው። የክርስትያን ወዳጆች ይሆኑና በስተመጨረሻው በእግዚአብሔር ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነተኛውን መልዕክት ስናጋራቸው የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ክርስቲያን ይሆናሉ።

ቤተሰቦቻችንን እና ዘመዶቻችንን ወደ ክርስቶስ በምንመራ ጊዜ ነገሮች አስቸጋሪ የሚሆኑት ለምንድነው? ለቤተሰቦችዎ ወይንም ለቅርብ ጓደኞችዎ ስለ ኢየሱስ በማካፈል ስኬታማ ሆናችኋል? የውይይት ቡድንዎን የሚጠቀም ማንኛውም መርሆዎች ካልዎ ያካፍሉ።

ሐምሌ 8
Jul 15

አስቸጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለመረዳት መሞከር


የሱስ አስቸጋሪ ሰዎችን በመረዳት በኩል እጅግ የተዋጣለት ነበር። በቃል እና በተግባሮቹ ተቀባይነት እንዳላቸው ይገልጽላቸዋል። የሚያስጨንቃቸውን ጉዳይ በጥሞና ያዳምጣል፣ ጥያቄን ያነሳል እናም ቀስ በቀስ የመለኮትን እውነት ይገልጣል። ልባቸው እጅግ ደንዳና በሆኑ ሰዎች ውስጥ ያለውን ውስጣዊ ናፍቆት ይረዳል እናም ከባድ ኃጢአተኞች ያላቸውን እምቅ ሀይል ይመለከታል።

በየሱስ በኩል ወንጌል ሊደርሰው የማይገባ ማንም ሰው የለም። የሱስ በእርግጠኝነት ይህንን ያምናል “ማንም ወድቆ ታች የቀረ፣ ማንም የቆሸሸ ሰው የለም እነዚህ ግን በክርስቶስ ነጻ መውጣት ይችላሉ” Ellen G. White, the desire of Ages. P.258። የሱስ ከሌሎቻችን ይልቅ ሰዎችን በተለየ እይታ ነው የሚያየው። በእያንዳንዱ ሰብአዊ ዘር ውስጥ ቀድሞ ሲፈጠሩ የነበራቸውን የክብር ነፀብራቅ ይመለከታል። በቀጣይ ጊዜያት ምን የመሆን እድል እንዳላቸው ሃሳባቸውን ያነሳሳል ብዙዎችም በህይወታቸው እርሱ የሚጠብቅባቸውን ለማሳካት ተነሳስተዋል።

ማቴ.4፡18-19፤ ማር.12፡28-34 እና ሉቃስ 23፡39-43ን አንብቡ። የሱስ ለጴጥሮስ እና ዮሐንስ ያቀረበው ተማጽኖ፤ ጥያቄ ሲያነሱበት ለነበሩ ፀሐፍት እና በመስቀል ላይ ለነበረው ወንበዴ ካቀረበው ተማጽኖ ጋር ምን ተመሳሳይነት ነበረው? ለእነዚህ ለእያንዳንዱ ጉዳይ ክርስቶስ የመረጠውን የአቀራረብ መንገድ ዐጢኑ። ከእናንተ የሚለየው ምን ነገር አለ?የሱስ በሄደበት ስፍራ መንፈሳዊ የሆነ እድሎችን ይመለከታል በጣም ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ለእግዚአብሔር መንግስት ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ያያል። ይህንን ችሎታ “ቤተክርስቲያንን የሚያሳድጉ አይኖች” ብለን እንጠራለን። ቤተክርስቲያንን የሚያሳድጉ አይኖች የሱስ እንደሚያይ ሰዎችን ለማየት እና ለእግዚአብሔር መንግስት ነፍሳት እንዲማረኩ ለማድረግ የሚያስችል መረዳት ነው። ይህ ደግሞ “ቤተክርስቲያንን የሚያሳድጉ ጆሮዎችን” ያካትታል። በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሊነግሩን ያልተቻላቸውን ፍላጎታቸውን ማድመጥን ይጠይቃል። በግልጽ ራሳቸውን መግለፅ ላልቻሉ፤ የሌላቸውን ነገር ግን ልባቸው የናፈቀውን ጉዳይ ማድመጥ መቻል ነው።

ጌታ በሌሎች ሰዎች ህይወት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ስሜት እንዲኖርዎ እንዲያደርግ ይጠይቁት። እግዚአብሔር ሁለተኛ መነካትን ሰጥቷችሁ እምነቶቻችሁን እንድታጋሩ በፊታችሁ ለዘረጋው መንፈሳዊ እድል አይኖቻችሁን እንዲገልጥ ፀልዩ።የሚያዩ አይኖች፣ የተጎዱ ልቦችን እንድናዳምጥ፣ ለምታውቋቸው ሰዎች በፈቃደኝነት ክርስቶስን እንድናካፈል፣ ስለ ፍቅሩ እንድናወራ እንዲያደርግ እግዚአብሔርን ጠይቁት ያኔ አስደናቂውን የህይወት ዘመን ጉዞ መጓዝ ትጀምራላችሁ። ከዚህ ቀደም ተለማምዳችሁ የማታውቁትን የእርካታ እና የደስታ ስሜት ታጣጥማላችሁ። ነፍሳትን ለማዳን የሚሰሩ ሰዎች ብቻ ናቸው ይህ ይዞ የሚመጣውን እርካታ የሚያውቁት።

ሐምሌ 9
Jul 16

ወሳኝ የሆኑ መልካም አጋጣሚዎችን መረዳት


የሐዋርያት ሥራ መፅሀፍ ደቀ መዛሙርቱ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋፋት በተጠቀሙበት የመልካም አጋጣሚ ታሪክ የተሞላ ነው። ከአንዱ የመጽሐፍ ጥግ እስከ ሌላኛው የቀደመችው ቤተክርስቲያን በውስጥ እና በውጪ ተግዳሮት ቢያጋጥማትም በሚደንቅ ሁኔታ እንዴት እያደገች እንደመጣች እናነባለን። 2ቆሮ.2፡12-13 ላይ ለአብነት ያክል ሃዋርያው ጳውሎስ በጢሮአዳ ስለነበረው ልምምድ ይነግረናል፤ “ስለ ክርስቶስም ወንጌል ወደ ጢሮአዳ በመጣ ጊዜ ለጌታ ሥራ በር ምንም ቢከፈትልኝ ቲቶን ወንድሜን ስላላገኘሁት መንፈሴ ዕረፍት አልነበረውም። ነገር ግን ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ።

” እግዚአብሔር ተኣምራዊ በሆነ መንገድ በአውሮፓ አህጉር ውስጥ ወንጌልን እንዲሰብክ በር ከፈተለት። ዛሬ እግዚአብሄር የከፈተው በር ነገ ሊዘጋ እንደሚችል ያውቃል። እድሉን በመጠቀም እና መልካም አጋጣሚውን በማየት ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ተጓዘ። የአዲስ ኪዳን አምላክ በር የሚከፍት አምላክ ነው። እምነታችንን እንድናጋራ መልካም አጋጣሚን የሚሰጥ ጌታ ነው። በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ በሙሉ እግዚአብሔር በሥራ ላይ ነው። በከተሞች፣ በአውራጃዎች፣ በየአገራት ከምንም በላይ በግለሰቦች ልብ ደረጃ የተከፈቱ በሮች ነበሩ።

ሐዋ.8፡26-38ን አንብቡ። እነዚህ ቁጥሮች ፊሊጶስ በእግዚአብሔር ምሪት እንዴት ክፍት እንደነበር እና መለኮታዊ ለሆነው መልካም አጋጣሚ የነበረው ምላሽ ምን ያስተምረናል?“መልአኩ የመራው ፊሊጶስ ብርሃንን የሚሻና ወንጌልን ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ነበር። ዛሬ መላዕክት መንፈስ ቅዱስ አንደበታቸውን እንዲቀድስ እና ልቦቻቸውን እንዲያከብር የሚሹ ሰራተኞችን ዱካ ይመራል። ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር የሚሠራበት መንገድ አይደለም። ሰዎች ለሌሎች ወዳጆቻቸው እንዲሰሩ የእርሱ እቅድ ነው።” Ellen G. White, The Acts of the Apostles, P. 109። የሚሰማ ጆሮ እና የሚያይ አይን ካለን ለእውነት መንግስት እውነትን የሚሹ ሰዎችን ለመድረስ የማይታዩት መላእክት ይመሩናል።

በዚህ ታሪክ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ማዕከላዊ እንደሆነ ተገንዘቡ። በዚህ ደረጃ ቃሉን የተረዳ ሰው ለሌሎች ለማሰራጨት ያለውን ወሳኝነትም ተረዱ። እዚህ ጋ ለኛ የምናገኘው ትምህርት ምንድነው?

ሐምሌ 10
Jul 17

0

ተጨማሪ ሐሳብ


Read Ellen G. White, `The Gospel in Samaria,` pp. 103-111, in the Acts of the Apostles. በዙሪያችን ያሉ ሰዎች በሙሉ ዘላለማዊውን ነገር ይሻሉ። የሱስ ተገቢ በሆነ መንገድ እንዳስቀመጠልን “መከሩስ ብዙ ነው ሰራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው “(ማቴ.9፡37)። ችግሩ ያለው መከሩ ላይ አይደለም። በመለኮት ሃይል በተቀቡ አይኖቹ የሱስ ያየውን እምቅ የሆነ የመከር ብዛት ደቀ መዛሙርቱ ያዩት የነበረው ተቃራኒውን ነበር። በዚህ ችግር ክርስቶስ የሰጠው ምላሽ ምን ነበር? “እንግዲህ የመከሩ ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው” (ማቴ.9፡38)። መፍትሄው ጌታ ወደ መከሩ እንዲልከን መጸለይ ነው።

ለምን ይሄንን ፀሎት አይፀልዩም ታዲያ “ጌታ ሆይ፤ ያንተን መንግስት ለማስፋፋት እንድትጠቀምብኝ እወዳለሁ” በየእለቱ ከፊት ለፊቴ ያስቀመጥክልኝን መልካም አጋጣሚ እንድመለከት አይኖቼን ክፈትልኝ። በየቀኑ ለማገኛቸው ሰዎች የተስፋን ቃል እና ማደፋፈር እንዲሁም ያንተን ፍቅር እና እውነት እንዳካፍል አግዘኝ።” ይህን ፀሎት ከፀለያችሁ እግዚአብሔር እንግዳ የሆነን ነገር በህይወታችሁ ላይ ያከናውናል።


የመወያያ ጥያቄዎች1.አንድ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ነፍሳትን ወደ የሱስ ማምጣት ስራ ላይ መሰማራት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። አይደለም እንዴ! አዎ እግዚአብሔር ብቻ ነው ልቦችን ሊለውጥ የሚችለው ነገር ግን በጥበቡ የዚህ ሂደት አካል እንድንሆን እኛን መጠቀም ስለፈለገ ጠርቶናል። ለአንዲትዋ ነፍስ መስራት ጊዜን፣ ጥረትን፣ ትዕግስትን እና ከላይ የመጣ ፍቅርን ይጠይቃል። ለክርስቶስ ውጤታማ ምስክር ለመሆን ለራስ መሞት ያስፈልጋል ይህ እንዲሆን ምን አይነት ምርጫዎችን ሊያደርጉ ይችላሉ?

2.የምታገኙዋቸው የሱስን የማያውቁ አንዳንድ ሰዎች እነማን ናቸው? ለነርሱ ለመመስከር ምን አድርጋችኋል? ወይንም ምን እያደረጋችሁ ነው? አልያም ወደፊት ምን ማድረግስ አለባችሁ? ስለ ተርሴሱ ሳውል አስቡ። ማንም ይለወጣል ብሎ ሊያስበው የማይችል ሰው ነው! ነገር ግን በእርሱ ላይ የሆነውን እናውቃለን። ይህ በውጫዊ እይታ ፈጥኖ ሌሎች ላይ የመፍረድ አደገኛነትን እንዴት ይነግረናል?

3.የሳውልን ታሪክ በልቦናችን እንደያዝን ማቴ.7፡6 በምናገኘው ጥቅስ ላይ ምን ልንል እንችላለን? “በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ እንቁዎችንም በእርያዎች ፊት አትጣሉ።”