የእግዚአብሔርን ተልዕኮ በማካፈል የሚገኝ ደስታ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 3ኛ ሩብ ዓመት 2020

ከሰኔ 20-26

1ኛ ትምህርት

Jun 27 - Jul 03
ምስክርነት ለምን?ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡- ያዕ.5፡19-20፤ ሉቃስ 15፡6፤ ሶፎ.3፡17፤ ዮሐ.7፡37፤ 1ጢሞ. 2፡3-4፤ 2ቆሮ 5፡14-15።


የሣምንቱ ጥናት መሪ ጥቅስ፡ “ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።”(1ጢሞ. 2፡3-4)

የ እግዚአብሔር ትልቅ ናፍቆት በሁሉ ስፍራ ያሉ ሰዎች ለፍቅሩ ምላሽ እንዲሰጡ፣ ፀጋውን እንዲቀበሉ በመንፈሱ እንዲለወጡና ድነው ወደ መንግስቱ ይገቡ ዘንድ ነው። ከኛ ድነት በላይ ሌላ የላቀ መሻት የለውም። ፍቅሩ ገደብ የለሽ ነው። ምህረቱም ከልኬት ሁሉ ያለፈ። ርህራሄው የማያልቅ። ይቅርታው ደግሞ የማያባራ። ሀይሉ መጨረሻ የሌለው። መስዋዕትን ከሚሹ ጨካኝ ከሆኑት አማልክት በተቃራኒ አምላካችን አስደናቂ መስዋዕት ሆነ። ምንም ያክል ለመዳን ብንፈልግ እግዚአብሔር የበለጠ ሊያድነን ይናፍቃል። “ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።” (1ጢሞ. 2፡3-4)። የርሱ የልቡ ናፍቆት የእናንተና የእኔ ድነት ነው።

ምስክርነት ሁሉ ስለ የሱስ ነው። እኛን ለማዳን ስላደረገው ነገር እንዴት ሕይወታችንን እንደለወጠው እና አስደናቂ ስለሆነው ቃሉ ነው ይህም እርሱ ማን እንደሆነ እና የእርሱን ውስጣዊ የሆነ ባህሪ ይነግረናል። ምስክርነት ለምን? እርሱ ማን እንደሆነ ስናስተውል፣ የፀጋውንና የፍቅሩን ሃይል አስደናቂነት ስናጣጥም ዝም ማለት አንችልም። ምስክርነት ለምን? ከርሱ ጋር በሥራው ስንካፈል ሰዎች በፀጋው ሲድኑና በፍቅሩ ሲለወጡ በማየት ወደሚገኝ ሀሴት እንገባለን። የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለሰኔ 27 ሰንበት ተዘጋጁ።ሰኔ 21
Jun 28

ለድነት እድልን መስጠት


እግዚአብሔር በየዕለቱ በየሥፍራው ያሉ ሰዎች እርሱን እንዲያውቁ እድልን ይሰጣቸዋል። በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ልቦቻቸውን ያነሳሳል። ተፈጥሮአዊ በሆነ አለም ረቂቅነት ውስጥ ራሱን ውብ አድርጎ ገለፀ። የዩኒቨርስ ስፋት፣ ስርአት፣ የተመጣጠነ ቅርጽና ይዘት ወሰን የለሽ ስለሆነው እና ተዝቆ የማያልቅ ጥበብ ስላለው ብሎም ሃይሉ ገደብ ስለሌለው አምላክ ያወራል። በህይወታችን ውስጥ ሁኔታዎችንና የእርሱን ፈቃድ በማመቻቸት ወደራሱ ይስበናል።

ምንም እንኳን እግዚአብሔር ራሱን አስደናቂ በሆነው መንፈሱ፣ በተፈጥሮ ሞገስ እና በርሱ የፈቃዱ ተግባር በኩል ቢገልጥልንም በጣም ግልጽ የሆነው የፍቅሩ መገለጥን የምናገኘው በክርስቶስ ህይወት እና አገልግሎት በኩል ነው። የሱስን ለሌሎች ስናካፍል ለመዳን እንዲሆንላቸው ትልቁን እድል ነው የሰጠናቸው። ሉቃስ 19፡10ን አንብቡ እና ከያዕ.5፡19-20 ጋር ያነጻፅሩ። የሉቃስ ወንጌል ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ስለመምጣቱ አላማ ምን ያስተምረናል? የጠፉትን በማዳን በክርስቶስ ስራ ላይ የምንተባበረው እንዴት ነው?ያዕቆብ እንዲህ ይላል “ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ።” (ያዕ.5፡20)። የሮሜ መፅሐፍም ይህንን እሳቤ ያጎላል፤ ሮሜ 1 እና 2 ላይ እግዚአብሔርን በተፈጥሮ ያዩ አሕዛብ እና በቃሉ አማካኝነት የእግዚአብሔርን ትንቢታዊ መገለጥ የተቀበሉ አይሁዶች ሁለቱም ያለ ክርስቶስ ሆነው ጠፍተዋል።

ሮሜ 3-5 ላይ ጳውሎስ ድነት የሚገኘው በጸጋ በእምነት ብቻ እንደሆነ ይገልጽልናል። ሮሜ 6-8 ላይ እያንዳንዱን አማኝ ያፀደቀው ፀጋ ራሱ እንዴት እንደሚቀድሰንም ይነግረናል። ሮሜ 10 ላይ እንዲህ ይለናል “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።” (ሮሜ 10፡13)። ከዛም እንዲህ ይለናል ካላመኑ ሊጠሩ አይችሉም፤ ካልሰሙ ደግሞ ሊያምኑ አይችሉም፤ አንድ ሰው ካልነገራቸው ደግሞ ሊሰሙ አይችሉም። በድነት እቅድ ውስጥ በወንጌል ክብር የጠፉ ሰዎቹን ልንደርስ ከእግዚአብሔር ጋር ተያይዘናል።

ለሰዎች የምንሰጠው ምስክርነት የመዳን ብቸኛው እድል አይደለም። መስከረን የምንሰጣቸው እጅግ ምርጡን እድል ነው። በእግዚአብሔር የሰውን ዘር የመዋጀት እቅድ ውስጥ የኛ ሚና ምንድነው? ስለዚህም ጉዳይ እስቲ አስቡ፡- ምን ያህል ሰዎች ከእርስዎ አንደበት ወንጌልን ሰምተዋል?

ሰኔ 22
Jun 29

የሱስን ማስደሰት


ሰዎች እንዲህ ብለው ጠይቀዋችሁ ያውቃሉ “ቀኖቻችሁ እንዴት እየሄዱላችሁ ነው?” “ዛሬ ሁሉም ነገሮች ጥሩ ሆነውላችኋልን?” እግዚአብሔርን ልክ እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎችን ብንጠይቀው “እግዚአብሔር፣ ቀኖችህ እንዴት እየሄዱልህ ነው? ምን አይነት ምላሽን የምታገኙ ይመስላችኋል ምናልባት ይህን የሚመስል ምላሽ ሊሰጠን ይችላል። “ቀኖቼ በጣም አስቸጋሪ ነበሩ። አንድ ሺህ የሚሆኑ ስደተኞች በካምፕ ውስጥ በቅዝቃዜ፣ በረሃብ፣ ህጻናት ሲያለቅሱ ሳይ አይኖቼ በእንባ ተሞሉ።

በህዝብ የተጨናነቁ የአለማችን ከተሞች ላይ ተራመድኩ ቤት አልባ እና ምስኪኖችን ሳይ አነባሁ። በተጠቃች ሴት እና ለወሲብ ባርነት ስትሸጥ ፈራ ተባ ባለች ሴት ልቤ በጣም ተሰብሯል። አውዳሚ የሆነ ጦርነትን፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን አጥፊነት ውጤት እና በስቃይ የሚያዝለውንና ለሞት የሚያበቃውን ህመም ተመልክቻለሁ።” “ግን እግዚአብሔር አንተን የሚያስደስትህስ ነገር አለን? ለልብህ ደስታን የፈጠረልህስ ምን ነገር አለ? እንድትዘምር ያደረገህስ ምን ነገር አለ? ሉቃስ 15፡6፣ 7፣9፣10 እና 22-24፣ 32ን አንብቡ፡፤ እነዚህ ታሪኮች እንዴት ተጠናቀቁ እነዚህ የታሪክ ፍጻሜዎች ስለ እግዚአብሔር ምን ይነግሩናል?የጠፉት ሲገኙ መላው የሰማይ ደስ ይሰኛል። በሽታ፣ አደጋና ሞት በበዛበት በዚህ አለም ላይ የእግዚአብሔርን ልብ የምናስደስተው የድነትን “መልካም የምስራች” ለሌሎች ስናጋራ ነው። የክርስቶስን ፍቅር እንድናጋራ የሚያነቃቃን አንዱና ትልቁ ነገር ምስክርነት የእግዚአብሔርን ልብ እንደሚያስደስተው የምናውቀው እውቀት ነው። ሁልጊዜ ፍቅሩን ስንገልጥ መላው ሰማይ ይዘምራል።

ሶፈ. 3፡17ን አንብቡ። የሚያድነውን የርሱን ፀጋ ስንቀበል የጌታችን ምላሽ ምን ይሆናል?ይህንን ትዕይንት እስቲ አስቡ። በእናንተ ምስክርነት ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ወይንም ወንዶች ወይንም ሴቶች የሱስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ተቀበሉ። የሱስ ደስ ተሰኘ። መላው የሰማይ ሰራዊት በሃሴት መዝሙር ወደፊት መጡ ታላቁ አዳኛችንም በዚህ ግለሰብ ተደስቶ የደስታውን ዝማሬ ተቀላቀለ። ምስክርነታችን ሀዘን በሞላበት አለም ውስጥ ለእግዚአብሔር ልብ ደስታን እንዳመጣ ሁሉ እንዲህ ያለ የበለጠ ሽልማትና የበለጠ እርካታ የሚያመጣ ምን ነገር አለ?

ሰኔ 23
Jun 30

በመስጠት ማደግ


የሙት ባህር የምድርን የታችኛውን ክፍል ያሳየናል። ከባህር ጠለል በታች 1388 ጫማ በመሆን የአለም ታችኛው የባህር ክፍል ሆኖ ተቀምጧል። የዮርዳኖስ ወንዝ ከገሊላ ባህር ይነሳና በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል ተገፍቶ መጨረሻውን ሙት ባህር ላይ ያደርጋል። ሙቀት፣ ደረቅ ያለው የአየር ንብረት ከሚያቃጥለው የጸሐይ ብርሃን እና የበረሃማነት ሁኔታ ጋር ሲደመር ውሃው በፍጥነት እንዲተን ያደርገዋል። የሙት ባህር ጨዋማነት እና የማዕድናት ይዘት 33.7 ፐርሰንት ስለሆነ በውሃ ውስጥ ትንሽ ይቆያል። አሳዎች የሉትም፣ እፅዋትም የሉትም ስር ላይ ብቻ ጥቂት ማይክሮብስ እና ባክቴሪያዎች ናቸው ያሉት።

በክርስትና ህይወታችን ወደኛ ህይወት የፈሰሰው የእግዚአብሔር ፀጋ ወደሌሎች መፍሰስ ካልቻለ የማንንቀሳቀስ እና እንደ ሙት ባህር ህይወት የለሽ እንሆናለን። እንደ ክርስቲያንነታችን ግን እንዲህ አይደለም ልንኖር የሚገባን። ዮሐ.7፡37-38 እና ሉቃስ 6፡38ን አንብቡ። ከሙት ባህር ልምምድ በተቃራኒው አማኞች ከክርስቶስ የሚፈሰውን የህይወት ውሃ ምንጭ ተቀብለው ሲደሰቱ ተፈጥሮአዊ ውጤቱ ምን ይሆናል?“እግዚአብሔር ያለ እኛ እገዛ ሀጢያተኞችን በራሱ መንገድ መድረስ ይችላል። ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ያለ መልካም ባህልን እናዳብር ዘንድ የእነርሱን ስራ እንጋራለን። ወደ ደስታው እንገባ ዘንድ፣ በእርሱ መስዋዕትነት ነፍሳት ሲድኑ ያለውን ደስታ በመመልከት። በድነት ስራው ውስጥ እኛም ልንሳተፍ ይገባናል። “ባለ ድል ሊሆኑ የሚወዱ ሁሉ ከራሳቸው ሃሳብ ሊወጡ እና ይህንን ታላቅ ሥራ ሊፈጽሙ የሚችሉበት ሁኔታ ቢኖር ስለ ሌሎች ድነት ጥልቅ የሆነ መሻት ሲኖራቸው ብቻ ነው” Ellen G. White, Fundamentals of Christian Educaiton, P. 207:: የሱስ በሕይወታችን ያደረገውን ለሌሎች ስናካፍል እናድጋለን።

በክርስቶስ የተሰጠንን ነገር ሁሉ ከግምት ውስጥ እናስገባ ያ ካልሆነ ግን እጅግ አሰቃቂ ራስ ወደድነት ስለሚጠናወተን የተሰጠንን ነገር እንዳናጋራ ያደርገናል። በዚህ መንገድ እምነታችንን ካላጋራን መንፈሳዊ ህይወታችን ልክ እንደ ሙት ባህር እዛው ቆሞ ይቀራል። ለሌሎች በመመስከር፣ ለሌሎች በመፀለይ እና የሌሎችን ፍላጎት በማገልገል ዙሪያ የእናንተ ልምምድ ምን ነበር? እነዚህ ልምምዶች እምነታችን ላይ ተፅዕኖን ያመጡት እና ከጌታ ጋር እንድራመድ ያደረጉን እንዴት ነው?

ሰኔ 24
Jul 01

ለክርስቶስ ትእዛዝ ታማኝ መሆን


ለክርስቶስ ታማኝ መሆን ለፈቃዱ ቁርጠኛ መሆንን ይጠይቃል። ትዕዛዛቱን መታዘዝ ይፈለግብናል። ውጤቱም የጠፉትን ለማዳን ልቡ ሲመታ ልባችንም አብሮ ይመታል። እርሱ ቅድሚያ የሰጠውን ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጠው ያደርጋል።

1ጢሞ.2፡3-4 እና 2ጴጥ.3፡9ን አንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚአብሄር ልብ ምን ይነግሩናል? ቅድሚያ የሚሰጠው ነገርስ ምንድነው?እግዚአብሔር ሰዎችን ለማዳን ልቡ ይቀጣጠላል። ከዚህ የበለጠ ለእርሱ ሌላ አስፈላጊ ነገር የለም። የእርሱ የልብ ጉጉት ‹ሁሉ› ይድኑ ዘንድ እና ‹እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ› ነው (1ጢሞ. 2፡4)። እርሱ “ሁሉ ወደ ንስሃ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሳል” ይለናል (2ጴጥ 3፡9)። ስለዚህ ጥቅስ - The SD Bible Commentary, ሲናገር የግሪኩ ቃል `willing` ለሚለው ቃል የተጠቀመው ቦውሎማይ `boulomai` ሲሆን የሚገልፀውም የልብን ዝንባሌ “ፍላጎት” ወይንም “መመኘት”ን ነው።

ማጣቀሻው “ግን” የሚለውን ቃል ሲጠቅስና ሲያብራራ በግሪኩ አጠራር ግን `but`ን አላ `alla` ነው የሚለው። እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው “የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ በስህተት ተረድተው እርሱ አንዳንዶች እንዲጠፉ ይወዳል ለሚሉ ተቃራኒ የሆነ አጽንዖትን ለመስጠት እና ሁሉ ይድኑ ዘንድ እንደሚሻ ለማረጋገጥ ነው” - The SD Bible Commentary vol. 7 p.615። ለእያንዳንችን የክርስቶስ ትዕዛዝ ምስክር በመሆን የእርሱን ፍቅር፣ ፀጋ እውነት እንድናጋራ ሲሆን ይህ ደግሞ የሰው ልጆች ሁሉ እንዲድኑ ያለውን የርሱን ከፍ ያለ መሻት ያሳያል። ሐዋ.13፡47 አንብቡ እና ከኢሳ.49፡6 ጋር ያነጻጽሩ። ይህ ጥቅስ በእነማን ላይ ነው ተግባራዊ የሆነው? ጳውሎስ እንዴት አድርጎ ነው ይህንን ጥቅም ላይ ያዋለው?የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ከአንድ በላይ የሆነን ነገር የሚያመለክቱበት ጊዜያት አሉ። እዚህ ጋ ሃዋርያው ጳውሎስ ትንቢቱ እስራኤል እንደሚያመልክ በቅድሚያ ስለ መሲሑ ትንቢት ከተናገረ በኋላ (ኢሳ.41፡8፤ ኢሳ.49፡6 እና ሉቃስ 2፡32ን ተመልከቱት) ከዛም ትንቢቱን ለአዲስ ኪዳንዋ ቤተክርስቲያን ተግባራዊ አድርጎ ጠቀሰ። ቤተክርስቲያን የክርስቶስን ትዕዛዝ ችላ ስትልና መታዘዝዋን ስትቀንስ የመኖርዋን አላማ እየጣለች እና ለአለም የተሰጣትን ትንቢታዊ ጥሪዋን እያጣች ነው። ለቤተክርስቲያናት፣ የበለጠ ወደ ውስጥ ጠጋ ስንል ደግሞ ለአጥቢያ ቤተክርስቲያናት አላማን የመርሳት አደገኝነቱ ምን ያክል ነው?

ሰኔ 25
Jul 02

በፍቅር መነሳሳት


በዚህ ሳምንት ጥያቄዎችን መመለስ ላይ ትኩረት እናደርጋለን፤ “ምስክርነት ለምን?” እምነታችንን ስናጋራ እግዚአብሔር ለዚህች ምድር ካለው ተልዕኮ ጋር በመተባበር የምናገኘው ደስታ እንዳለ ተገንዝበናል። ስለ ፍቅሩ ያለን ምስክርነት ሰዎች የርሱን ጸጋና እውነት የበለጠ በግልፅ እንዲያዩ የድነት ታላቅ እድል መስጠት ነው። በተመሳሳይ ጊዜም ምስክርነት እግዚአብሔር በመንፈስ እንድናድግ የሚያደርግበት ዘዴውም ነው። ክርስቶስ ለኛ ያደረገልንን ለማካፈል እና ለሌሎች ለመመስከር ካቃተን እውነተኛ የሆነው መንፈሳዊ ህይወታችን ታንቆ እንዲያዝ ያደርግብናል።

ምስክርነት ሁሉም ሰብአዊ ዘር ይድን ዘንድ የሚናፍቅ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል። በተመሳሳይ መንገድ ለትዕዛዙ የምንመልሰው የመታዘዝ ምላሽ ነው። በዛሬው ትምህርታችን ለምስክርነት ሁሉ ታላቅ መነሳሳትን ስለሚሰጠን ነገር እናጠናለን። 2ቆሮ.5፡14-15፤ 18-20ን አንብቡ። ጳውሎስ ለወንጌል ሲል መከራን፣ ስቃይን ችግርንና ውጣውረድን እንዲለማመድ ያነሳሳው ነገር ምንድነው? ይህ ተመሳሳይ የሆነ መነሳሳት ለክርስቶስ ያለንን አገልግሎት እንድናፋጥን የሚያደርገው እንዴት ነው?ሐዋርያው ጳውሎስን ያነሳሳው ፍቅር ነው። ለሌላ ነገር ልታደርጉ የማትችሉት ለፍቅር ስትሉ ግን የምታደርጉት ነገር አለ። ሐዋርያው እንዲህ ይለናል “የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል” ይህ የነበረ ዘላለማዊ የሆነ እውነት ነው። ግድ ይለናል (ያስገድደናል) የሚለው ቃል `Constrains` ይገፋፋናል፣ ይቀሰቅሰናል፣ ይቆጣጠረናል ወይም በከፍተኛ ሁኔታ ያነሳሳናል” ማለት ነው። የክርስቶስ ፍቅር የጳውሎስን ተግባር ተቆጣጥሮታል ለምስክርነትም አነሳስቶታል። ለአላማው ተስፋ ሳይቆርጥ እና በልቡ ባይተዋርነት ሳይሰማው በሜዲትራኒያን የአለም ክፍሉ ሁሉ የድነትን እቅድ አካፈለ።

“ፍቅር በልባችን ሊኖር ይገባል። ሙሉ የሆነ ክርስቲያን ለተግባር የሚያነሳሳውን ነገር የሚያገኘው ለጌታው ካለው ልባዊ ፍቅር የመነጨ ነው። ለክርስቶስ ከስር መሰረቱ ያለው ጥልቅ ፍቅር ይመነጭና ለወንድሞቹ ራስ ወዳድነት የማይታይበት መሻት እንዲያድርበት ያደርጋል።” Ellen G. White, the Adventist Home, p. 42:: ክርስቶስ ለኛ ያደረገውን ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት በትክክል ስንረዳ በፍቅሩ እንጥለቀለቃለን እናም እርሱ ለኛ ያደረገልንን ነገር ለሌሎች ለማጋራትም እንገደዳለን። ሁሉን የፈጠረው (ጋላክሲዎችን፣ ከዋክብትን፣ መላዕክታት፣ መላውን ትዕንተ ዓለም እና ሌሎች አለማት) እርሱ ነው ለኛ ሲል በመስቀል ላይ የሞተው። ይህ አስደናቂ እውነት ታዲያ እንዴት ነው ለእግዚአብሔር ፍቅር እንዳይኖረንና ይህን ፍቅሩን እንድናጋራ መሻትን የማይሰጠን?

ሰኔ 26
Jul 03


ተጨማሪ ሐሳብ


Read Ellen G. White, `God’s purpose for His church, pp. 9-16, in the Acts of the Apostolics, and pp. 822-828 in the Desire of Ages. የአዲስ ኪዳንዋ ቤተክርስቲያን የመኖርዋን አላማ ያለመረዳትን አደገኛ ሁኔታ ተጋፍጣለች። ኤለን ጂ ኋይት ይህንን አደጋ ስትገልጽ እንዲህ ትላለች “በኢየሩሳሌም ባለችው ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰው ስደት የወንጌል ሥራ በኃይል እንዲከናወን አድርጓል። በዛ ስፍራ ላይ የወንጌል አገልግሎት ፍሬያማነትን አገኘ። ደቀ መዛሙርቱም አዳኙ ወደ ዓለም ሁሉ እንዲሄዱ የሰጣቸውን ተልዕኮ በመዘንጋት በዛ ስፍራ ረዘም ላለ ጊዜ የመቆየት አደጋ ላይ እንዲወድቁ አደረጋቸው። ክፉውን የመቃወም ጥንካሬ የሚገኘው ጠንካራ በሆነ አገልግሎት መሆኑን ስለዘነጉ የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያንን ከጠላት ጥቃት ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አስፈላጊ ስራ እንደሌላቸው ማሰብ ጀምረው ነበር። አዲስ የተለወጡ ሰዎች ላልሰሙት እንዲያጋሩ ከማስተማር ይልቅ በአከናወኑት ስኬት ረክተው በዛ የመቆየት አደጋ ውስጥ ወድቀዋል” – The Acts of the Apostles, p. 105.


የመወያያ ጥያቄዎች1.ኤለን ጂ ኋይት ከላይ የተናገረችውን በተለይ ደግሞ በመጨረሻ መስመር ላይ ያለችውን በጥንቃቄ ተመልከቱ። እኛም ዛሬ ተመሳሳይ የሆነ አደጋ ላይ እንዳንወድቅ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ለምንድነው? ከፊት ለፊታችን ያለው የሚሲዮናዊ ተግዳሮት ላይ ይህ አይነት አመለካት ለምንድነው አስፈሪ ብሎም አሳዛኝ ስህተት የሆነው?

2.እያንዳንዱ የወንጌል መጽሐፍ ሲያልቅ በተመሳሳይ ትዕዛዝ የሚያበቃው ለምን ይመስልዎታል? ማቴ.28፡18-20፤ ማር.16፡1516፤ ሉቃስ 24፡46-49፤ ዮሐ. 20፡21ን አንብቡ። በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ላሉ አማኞች ይህ ማለት ምን ማለት ነው፤ ዛሬ ላይ ላለን ለኛስ?

3.ምስክርነት እና አገልግሎት ለእውነተኛ መንፈሳዊነት አንዱ አንዱን ሊተካ ይችላልን? ከሆነ እንዴት አድርገን ነው ይህ ወጥመድ እንዳይሆንብን የምንጠነቀቀው?

4.በውይይት ክፍሎ ውስጥ፤ ምስክርነት እና አገልግሎት የራስዎ መንፈሳዊ እድገት ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያመጣ በማክሰኞ ትምህርት መጨረሻ ላይ ለሚገኘው ጥያቄ ያልዎትን መልስ ተነጋገሩ። ሌሎችን ሊያግዝ የሚችል የተማሩዋቸው ሌሎች ትምህርቶች ምንድናቸው? ሌሎችን ማገዝ ስትችሉ ያላደረጋችሁትና የሰራችሁት ስህተትስ ምን አለ?

5.እግዚአብሔር በየግላችን እንደሚወደን በተገለጠው አስደናቂ እውነታ ላይ ትኩረት አድርጋችሁ አስቡ። ይህንን ትርጉም እንዴት ያስተውሉታል? ምናልባትም ይህ በዩኒቨርስ ሁሉ ላይ ያለ በጣም ወሳኝ እውነት ሆኖ ህይወትዎ ላይ ተፅዕኖ የፈጠረብዎ እንዴት ነው?