ዕዝራ እና ነህምያ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2019

ህዳር 13-19

9ኛ ትምህርት

Nov 23 - 29
ፈተና፣ መከራ እና ዝርዝር ገለፃሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ። ዕዝራ 1፡9-11፣ ዳን1፡1-2፣ ዳን 5፣ ዘዳ30፡1-6፣ ዕዝራ 8፡1-23፣ ነህ 11፡1-2 ፣12፡1-26


መታሰቢያ ጥቅስ “በእግዚአብሄርም ባርያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሄር ህግ ይሄዱ ዘንድ፣ የጌታችንንም የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ሁሉ ፍርዱንም ስርዓቱንም ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ እርግማንና መሐላውን አደረጉ።”(ነህምያ 10፡29)

በ መፅሀፍ ቅዱስ የሚገኙትን የዘር ሀረግ እና ሌሎች ረዣዥም ዝርዝሮች ብዙ ጊዜ እንዘልላቸዋለን። እግዚአብሄር ግን እነዚህን ያካተተው በምክንያት ነው። የመፅሀፍ ቅዱሱ ጌታ የዝርዝር ጉዳዮች ጌታ ነው። ለትናንሽ ዝርዝሮች እንኳን ትኩረት መስጠቱ በእርሱ መቼም እንደማንረሳ ያረጋግጥልናል።

የዘር ሀረግ ዝርዝሮች እግዚአብሄር ስለ ቤተሰቦቻችን እንደሚያውቅ፣ የዕቃዎች ዝርዝር ደግሞ “ቦታ ለማይሰጣቸው” ነገሮች እንኳን እግዚአበሔር ግድ እንደሚለው ያውጃሉ። እግዚአብሔር ስለ ድንቢጥ ግድ እንደሚለውና የራሳችንን ፀጉር እንደሚቆጥር ኢየሱስ ተናግሯል። “አምስት ድንቢጦች በአስር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ እንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ የተቆጠረ ነው፤ እንግዲያስ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ።”(ሉቃ12፡6-7) ስለእነዚህ ትናንሽ ዝርዝሮች ግድ የሚለው አምላክ ስለ እኛም ግድ ይለዋል። የሚያስጨንቁንን ዝርዝር ነገሮች እንኳን ሳይቀር ያውቃል። በመሆኑም በሙሉ መተማመን በእግዚአብሔር ላይ እንዲሁም ስለ እያንዳንዱ የህይወታችን ክፍል ግድ እንደሚለው በማወቅ ልናርፍ ይገባናል። ይህ እኛን ከማፅናናትም ባሻገር ሰለ ዝርዝር ጉዳዮች ትኩረት መስጠት እንዳለብን ያስተምረናል። *የዚህን ሳምንት ትምህርት በማጥናት ለህዳር 20 ሰንበት ይዘጋጁ።

ህዳር 14
Nov 24

የታሪክ አምላክ


ዕዝራ 1፡9-11ን እና ዳን1፡1-2ን ያንብቡ። በዳንኤል ላይ የተጠቀሰው ጥቅስ ዕዝራ ስለምን እየተናገረ እንደሆን እንድናስተውል ይረዳናል?በዕዝራ መፅሀፍ ዝርዝሮች ሲሰጡ፤ በዳንኤል ላይ ደግሞ ዋናውን ምስል የሚሰጠንን ታሪክ መፃፉን አስተውሉ። እነዚህ ጥቅሶች በአንድነት ሲነበቡ እግዚአብሄር ሁሉን እንደሚቆጣጠር ያሳዩናል።

“የህዝቦች ታሪክ ዛሬ ለእኛ ምስክር ነው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ህዝብ እና ለእያንዳንዱ ግለሰብ በትልቅ ዕቅዱ ውስጥ ቦታ አዘጋጅቷል። የሰው ልጆች መንሹን በእጁ በያዘው ፍፁም አምላክ እየተፈተኑ ነው። ሁሉም በራሱ ምርጫ ዕጣ ፈንታውን ሲወስን እግዚአብሄር ደግሞ ዓላማው ይፈፀም ዘንድ ከላይ ሆኖ ይቆጣጠራል።”— Ellen G. White, Prophets and Kings, p.536 ዳንኤል 5ን ያንብቡ። እነዚህ ጥቅሶች በብልጣሶር ላይ ስለደረሰው ፍርድ ምን ያስተምሩናል?ባቢሎን የወደቀችው በ539 ዓ.ዓ. የሜዶንና ፋርስ ንጉስ ቂሮስ ድል በነሳ ጊዜ ነበር። ብልጣሶር በስኬቱ፣ በሀብቱ እና በስመጥርነቱ በከንቱ ከመመካቱ የተነሳ ሊሞት ባለበት ምሽት ልቅ የሆነ ግብዣ አሰናዳ። ቀኑ ተቆጥሮ ወደ ፍፃሜ እንደደረሰ የመለኮት እጅ በቤተ-መንግስቱ ግድግዳ ላይ ፃፈ። ምንም እንኳን የኃያሉን ንጉስ የናቡከደነፆርን ታሪክ መለወጥ ቢያውቅም፣ ከዚያ ግን ለመማር አልፈለገም። የእግዚአብሔርን ማስጠንቀቂያ ችላ ስንል እና መመሪያዎቹን ሳንከተል ስንቀር መጨረሻችን አሳዛኝ ይሆናል።

ነቢዩ ዳንኤል በዚያ የነበረ ቢሆንም ትኩረት ግን የሰጠው አልነበረም። የእግዚአብሔርን ቅድስና እና ሀልዎት ስንዘነጋ መንገዳችን በችግር እና በሀዘን ይሞላል፤ ፍፃሜውም ሞት ይሆናል። ዳንኤል የናቡከደነፆርን ታሪክ ለንጉሱ ብልጣሶር ከተናገረ በኋለ እንዲህ አለው፡“ብልጣሶር ሆይ አንተ ልጁ ስትሆን ይህን ሁሉ እያወቅህ በሰማይ ጌታ ላይ ኮራህ እንጂ ልብህን አላወረድህም።”(ዳን 5፡22) ብልጣሶር የሰራውን ስህተት እኛም በህይወታችን ላለመስራት ምን ማድረግ አለብን? የመስቀሉ እውነት ሁሌም በእግዚአብሄር ፊት ዝቅ ብለን እንድንኖር እንዴት ያስችለናል?

ህዳር 15
Nov 25

በከተሞቻቸው ውስጥ


በዕዝራ 2 እና በነህምያ 7 ላይ ያሉትን የስም ዝርዝሮች ተመልከቱ። ስለ እነርሱ ምን ታስተውላላችሁ?በዕዝራ ምዕራፍ 2 ላይ ያለው የስም ዝርዝር (ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋር ከባቢሎን የተመለሱ ምርኮኞች ዝርዝር) በነህምያ ምዕራፍ የተደገመው በምክንያት ነው። እነዚህ ዝርዝሮች ለእኛ አሰልቺ ቢመስሉም እግዚአብሔር እኛን ግድ ስለማይሉን ዝርዝሮች እንኳን እንደሚጠነቀቅ ያስተምሩናል።

የኢየሩሳሌም ቅጥር አሁን የተጠናቀቀ ሲሆን ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዝርዝር ሊያሳይ የፈለገው ነጥብ አለ። ይኸውም ምንም እንኳን እግዚአብሔር ብቻውን ስኬትን ቢሰጣቸውም በዕዝራና ነህምያ ትውልድ የተመለሱት የእስራኤል ልጆች ለዚህ ስራ አስተዋፅኦ ማድረጋቸውን ያሳየናል። ምንም እንኳን ስራው ውስብስብና በእንቅፋት የተሞላ እንዲሁም ከተመደበለት ጊዜ በኋላ የተጠናቀቀ ቢሆንም አዲሱ ትውልድ የተመሰረተው በቀደመው ትውልድ ስኬት ላይ ነበር።

የዕዝራ እና የነህምያ መሪነት ትልቅ ዋጋ የሚሰጠው ቢሆንም ህዝቡ ደግሞ የሚሰሩት ተግባር ነበራቸው። እያንዳንዱ ቡድን በተለያየ ጊዜ በተለያየ ስራ ላይ ቢሳተፍም ውጤቱ ግን አስገራሚ ነበር። ጅማሬው (ዕዝራ 2) ከፍፃሜው ጋር (ነህምያ 7) ጋር ይያያዛል። የተገነባው የኢየሩሳሌም ቤተ-መቅደስ ብቻ ሳይሆን ኢየሩሳሌም ራሷ ታድሳና ዳግመኛ ታንፃ ነበር። ነህምያ 7፡73ን ያንብቡ። የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለመፈፀም በነበራቸው ጥረት ስላገኙት ስኬት ምን እንማራለን?“እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ።” ከምርኮ መመለሳቸውን እና ዳግም ግንባታውን በብዙ መልኩ ስናየው አስደናቂ መሆኑን እንገነዘባለን። ከብዙ ዓመታት በፊት ከተማቸው ተደምስሶ፣ ቤተመቅደሳቸው ፈርሶ እና መሬታቸው ተረጋግጦ የነበሩ ህዝብ አሁን ወደዚያው መሬት እና ወደዚያው ከተማ ተመልሰው መቅደሱንም ጭምር ዳግመኛ ገነቡ። ለእነርሱ እና በዙሪያቸው ለነበሩ ህዝብ ተዓምራዊ እንደነበር አያጠራጥርም። ሁሉም ግን በእግዚአብሔር ፈቃድና እና የተስፋ ቃል ላይ የተመሰረተ ነበር። በህይወትዎ ውስጥ ተስፋ-የለሽ የሚመስል ግን እንደሚያሻግርዎ የተማመኑበት ምን ጉዳይ አለ? እግዚአብሔር

ህዳር 16
Nov 26

ካህናቱ የት ናቸው?


ትናንት እንደተመለከትነው የአይሁዳውያን ከባቢሎን መመለስ አስገራሚ የትንቢት ፍፃሜ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ሆኖም ግን ችግሮች መኖራቸው አልቀረም። አንዱ ትልቅ ችግር ከምርኮ ስለ መመለስ የተሰጡ ብዙ መልካም የተስፋ ቃሎች ቢኖሩም አንዳንድ አይሁዳውያን ግን ወደ አባቶቻቸው ምድር ለመመለስ አለመፈለጋቸው ነበር። በባቢሎን መቆየትን ምርጫቸው አደረጉ።ለምን ይሆን? ዕዝራ 8፡1-15ን ያንብቡ። በተለይም በቁ.15 ላይ ያተኩሩ። በዚህ ቦታ ትልቁ የትኩረት ነጥብ ምን ነበር? የእስራኤልን ህዝብ ወደ ምድራቸው እንዲመለሱ ለሚፈልግ ሰው ይህ ጉዳይ እንዴት የትኩረት ነጥብ ሊሆን ቻለ?እውነታው አንዳንድ በባቢሎን የነበሩ እስራኤላውያን ሌዋውያንንም ጨምሮ ለመመለስ አለመፈለጋቸው ነበር። ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙዎቹ ባቢሎን ምድር ተወልደው ያደጉ በመሆናቸው የሚያውቁት ሀገር ያንን ብቻ ነበር። ወደማያውቁት ምድር የሚደረገውን ረዥም እና አደገኛ ጉዞ ለመጓዝ ብዙዎች አልፈለጉ ይሆናል። በስተመጨረሻ ያወቅነው ነገር ቢኖር ብዙ ተግዳሮት ቢኖርም በቤተ-መቅደሱን ለማገልገል በቂ ቁጥር ያላቸው ሌዋውያን መመለሳቸውን ነው።(የሀሙሱን ትምህርት ይመልከቱ)

“አይሁዳውያን በምርኮ ምድር ሲኖሩ 150 ዓመት ሞልቷቸው ነበር። ከኒፑር ጉድጓድ ቁፋሮ የተገኙት ብዙ መዛግብት እንደሚያሳዩት በንጉስ አርጠክሴስ ዘመን በሜሶፖታምያ የሚኖሩ ብዙ ሀብታም አይሁዶች ነበሩ። ስለዚህም ለዕዝራና አብረውት ለነበሩ መሪዎች እነዚህን ሀብታም ሰዎች አብረዋቸው እንዲመለሱ ማግባባት ቀላል ስራ አይሆንም ነበር። እነዚህ ምርኮኞች በሀገራቸው የሚጠብቃቸው ነገር ከባዶ ተነስቶ ለመስራት የሚያስገድድ ከባድ ህይወት እና በባቢሎን ከለመዱት ያነሰ ምቾት ነበር። እነዚህን ነገሮች ስንመለከት ዕዝራ 2000 የሚሆኑ ቤተሰቦችን ዕድላቸውን በሀገራቸው ከወንድሞቻቸው ጋር እንዲያደርጉ ማሳመኑ አስገራሚ ይሆናል።”—The SDA Bible Commentary, vol.3, p.376. “በብዙ መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ልንገባ ያስፈልናል”(የሀዋርያት ስራ 14፡22)። እግዚአብሔርን በታማኝነት ማገልገል የሚፈልጉ ስለሚገጥማቸው መከራ እና ፈተና ምን ያስተምረናል?

ህዳር 17
Nov 27

ራስን በእግዚአብሔር ፊት ማዋረድ


ዘዳግም 30፡1-6ን ያንብቡ። ለዕብራውያን የተሰጠው የተስፋ ቃል ምን ነበር?ይህ እና ይህን የመሰሉ ሌሎች የተስፋ ቃላት ዕዝራና ነህምያን ለመሳሰሉ ሰዎች ምን ትርጉም አላቸው?ዕዝራ እና ነህምያ ትንቢቶችን ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። እግዚአብሔር ህዝቡን ከምርኮ እንደሚመልስ ያውቃሉ። በነህምያ 9 እንደተመለከትነው ታሪካቸውንና የችግሮቻቸውን ምንጭ ተገንዝበው ነበር። ሀጢዓተኛ ቢሆኑም የእግዚእሔርን ምህረትና ምሪትም ተረድተው ነበር።

በመሆኑም ከምርኮ ነፃ እንደሚያወጣቸው በአምላካቸው ላይ ታመኑ። እነዚያ የተስፋ ቃላት በመንገዳቸው ተግዳሮት እንደማይገጥማቸው ዋስትና የሚሰጡ አልነበሩም። በዚህ ሩብ ዓመት ጥናታችን በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ውስጥ እንኳን ሆነው የገጠማቸውን ፈተና እና መከራ ተመልክተናል።

ዕዝራ 8፡16-23ን ያንብቡ። የገጠማቸው ተግዳሮት ምን ነበር? ምን ምላሽስ ሰጡ?ዕዝራ በእግዚአብሔር ተስፋ ቃሎች ቢታመንም ጉዞው አደገኛ መሆኑን ተገንዝቦ ነበር። ስለዚህ ፆምና በእግዚአብሔር ፊት ራስን ማዋረድ ለስኬታቸው ምን ያህል በእግዚአብሔር ላይ ጥገኛ መሆናቸውን የሚገነዘቡበት መንገድ ነበር። በፊታቸው የሚገጥማቸውን አደጋ በማሰብ ዕዝራ ነህምያ እንዳደረገው (ነህ 2፡9)ንጉሱን እርዳታ ለመጠየቅ አስቦ ነበር። በመጨረሻ ግን ላለመጠየቅ ወሰነ። ቢጠይቅ ኖሮ እግዚአብሔርን አለማስከበር ይመስላል ብሎ አስቦ ይሆናል። ምክንያቱም ለንጉሱ እንዲህ ብሎ ተናግሮ ነበር፡- “የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኃይሉና ቁጣው ግን እርሱን በሚተው ሁሉ ላይ ነው።”(ዕዝ ፡22) ዕዝራም እግዚአብሄር እንደጠበቃቸውና በሰላምም እንደደረሱ በመፃፉ (ዕዝ 8፡31) ጉዳዩ በስኬት እንደተጠናቀቀ እናያለን።

በሁሉም ነገር በእግዚአብሔር መታመን እንዳለብን እርግጥ ነው። ሆኖም ከእኛ እምነት ውጪ ያሉ ሰዎችን እንኳን እርዳታ መጠየቅ የሚገባን መቼ ነው? ይህን ማድረግ ስህተት የማይሆነው አልፎ ተርፎም ተገቢ የሚሆነው ለምንድን ነው?

ህዳር 18
Nov 28

በቅድስት ከተማ ውስጥ


ነህምያ 11፡1-2ን ያንብቡ። ምን እየተካሄደ ነው? በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን በሌላ ከተማ ከሚኖሩት ለመለየት ዕጣ ማውጣት ያስፈለገው ለምንድን ነው?ነህምያ 11 ምን ያስተምረናል? ከስደት ከተመለሱት ውስጥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ማግኘት አስፈላጊ ነበር። በጊዜው በከተማ ከመኖር በገጠር መኖር የተሻለ ነበር። ህዝቡ ከአባቶቻቸው የወረሱት የራሳቸው መሬት ነበራቸው። ርስታቸውን ትተው ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ መኖር ከርስታቸው መነቀል አድርገው ይቆጥሩት ስለነበር ትልቅ መስዋዕተነትን የሚጠይቅ ሆነባቸው። ህይወት አዳዲስ ተግዳሮቶችን የያዘ ሲሆን በከተማ መኖርም በገጠር ከመኖር የተለየ ነው። በአዲስና ባልተለመደ ቦታ መኖር ሁሌም ያስቸግራል። ወንጌል ሊዳረስበት ወደሚያስፈልግ አዲስ ከተማ ወይም ሀገር ሄዶ መኖር ምን ያህል ከባድ ይሆን? በከተሞች ውስጥ የሚኖር ተልዕኮ አዲስ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል።

“ሰራተኞቻችን መድረስ የሚገባቸውን ያህል ሰዎችን እየደረሱ አይደለም። መሪዎቻችን ስራውን በንቃት አልመሩም። ዳግም ስለሚመለሰው አዳኝ መስማት የሚገባቸው ብዙ ሺህ ሰዎች ባሉበት ከተሞች የሚደረገው እጅግ ውስን ጥረት ያሳስበኛል። ይህን ጊዜም ለሚጠፉ ነፍሳት ከፍተኛ የሆነ የክርስቶስ ፍቅር ያላቸው እንዲሁም የመንፈስን ኃይል የታጠቁ ወንዶችና ሴቶችን ለተልኮው ሲጓዙ ማየት በጥብቅ እናፍቃለሁ።”— Ellen G. White, Testimonies for the Church, vol.7. p.40 በነህምያ 12፡1-26 ላይ ረዥም የካህናትና የሌዋውያን ዝርዝር ለምን ተካተተ?በእነርሱና በምዕራፉ ሁለተኛ ክፍል በተጠቀሰው (ነህ 12፡27-41) የኢየሩሳሌም ምርቃት መካከል ምን ግንኙነት አለ?

እግዚአብሄር ነገሮች በስርዓት እንዲተገበሩ ይፈልጋል። ትልልቅ ስኬቶች ከመከናወናቸው በፊት የተቀደሱ እና ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ያስፈልጋሉ። እነዚህ የካህናት ቤተሰቦች ከውጪ ጣልቃ-ገብነት በፀዳ ሁኔታ እግዚአብሄርን ያመልኩ ዘንድ የሚያግዙዋቸውን ቅጥሮች ከነህምያ ጋር አብረው ገነቡ። ቅጥሮች ለጥበቃ አስፈላጊ ቢሆኑም ያለ ካህናት ግን እወነተኛ አምልኮ ማካሄድ አይቻልም። ስለዚህ የተለያየ ስራ ያላቸው ሰዎች ሁሉ የየራሳቸው ሚና ነበራቸው።

ህዳር 19
Nov 29


ተጨማሪ ሀሳብ


Ellen G. White, “The Test of Discipleship,” pp.57-65, in Steps to Christ. “የክርስቶስን የፍቅር ይቅርታ ተረድተው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን እየፈለጉ ነገር ግን ፍፁም ካልሆነው ባህርያቸውና በውደቀት ከተሞላው ህይወታቸው የተነሳ ልባቸው በመንፈስ ቅዱስ መታደሱን እንኳን የሚጠራጠሩ አሉ። ለእነዚህ ሰዎች እንዲህ እላለሁ፤ ተስፋ አትቁረጡ። ከስህተቶቻችንና ከውድቀታችን የተነሳ በክርስቶስ እግር ስር ተንበርክከን የምናለቀስባቸው ብዙ ጊዜያት ይኖራሉ። ነገር ግን ተስፋ ልንቆርጥ አይገባንም። ጠላታ ቢያሸንፈን እንኳን የማንፈለግ የተጣልን እና በእግዚአብሔር የተተውን አይደለንም።በፍፁም! ክርስቶስ በአብ ቀኝ ሆኖ ስለ እኛ ይማልዳል…ወደራሱ ሊመልሳችሁ፤የራሱን ቅደስና እና ንፅህና በእናንተ ውስጥ ሊያይ ይፈልጋል። ራሳችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ ብትሰጡ በእናንተ መልካምን ስራ የጀመረው እስከ ዳግም ምፅዓቱ ድረስ ይቀጥለዋል። ተግታቸሁ ፀልዩ፤በሙላት እመኑ። በራሳችን መታመንን መተው እየተለማመድን በአዳኛችን ሀይል መታመንን እንቀጥል። የፊታችን መድሀኒት የሆነውን አምላካችንን እናመሰግነዋለን።”—Ellen G. White, Steps to Christ, p.64


የመወያያ ጥያቄዎች
1.ዳንኤል በትንቢተ ዳንኤል ምዕ. 2 ላይ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት የመንግስታትን መውደቅና መነሳት እንዲሁም የዘመናችን አውሮፓ አንድ ያለመሆንን ክስተት ያለ ስህተት መተንበዩን አስቡ። በዚህ ውጥንቅጥ በሞላው ዓለም ውስጥ እግዚብሔር ሁሉን እንደሚያውቅ እና አስቀድሞ እንደተናገረ ማወቃችን ምን ዓይነት መፅናናትን ይሰጠናል?
2.እግዚብሔር ስለ እኛ ሁሉን ያውቃል። በዚህም መፅናናትን እና ድፍረትን፣ በእርሱም መታመንን እናገኛለን። “አሁንም ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፤እስራኤልም ሆይ የሰራህ፣ እግዚብሔር እንዲህ ይላል፡- ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ”(ኢሳ 43፡1)። በማህበራዊ ግንኑነት፣ በገንዘብ፣ በስሜት ወይም በተለያየ ቀውስ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ጥበቃና እና ጥንቃቄ እንዴት ልታረጋግጡላቸው ትችላላቸሁ?
3.በረቡዕ ክፍል ላይ ዕዝራ ከንጉሱ ጥበቃና እርዳታ መጠየቅ ያልፈለገው ስለ እግዚብሔር ጥበቃ የተናገርኩትን ከንቱ እና ባዶ ንግግር ያስመስልብኛል ብሎ ማሰቡን በድጋሚ ይመልከቱ። ለምሳሌ እግዚአብሔር ፈዋሽ መሆኑን እናውቃለን። ነገር ግን ይህ ማለት ወደ ሀኪም በምንሄድበት ጊዜ እግዚኣብሄርን እንደማናምነው እየመሰከርን ነው? ይህን ሃሳብ በክፍል ውስጥ ይወያዩበት።