ዕዝራ እና ነህምያ
የጎልማሶች ሰንበት ትምህርት
የመጸሐፍ ቅዱስ ጥናት መምሪያ - 4ኛ ሩብ ዓመት 2019

ህዳር 20-26

10ኛ ትምህርት

Nov 30 - Dec 6
እግዚአብሔርን ማምለክሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት ጥናት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፡- ነህ. 12:27-47፣ 1ኛ ዜና 25:68፣ 1ኛ ዮሐ. 1፡7-9 ፣ ዮሐ. 1:29፣ 36፣ 1ኛ ቆሮ. 5:7፣ ዕብ. 9:1-11፡፡


መታሰቢያ ጥቅስ "ቸር ነውና፥ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እያሉ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በእርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤የእግዚአብሔርም ቤት ስለተመሠረተ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በታላቅ ድምፅ እልል አሉ። ዕዝ 3:11

የ ዚህ ሳምንት መታሰቢያ ጥቅስ የዕብራውያንን የአምልኮ ልምድና ለእግዚአብሔር ያላቸው ምስጋና እንዴት ጥልቅ ሆኖ እንደሚፈስ ያሳየናል። በ515 ዓ.ዓ የአዲሱን ቤተመቅደስ ምርቃት አከበሩ (ዕዝ 6:15-18) በመቀጠል ከአንድ ከስልሳ ዓመታት በኋላ ህዝቡ የእየሩሳሌምን ቅጥር መጠናቀቅን ምርቃት በዓል አከበሩ (ነህ 6:15 – 7:3፣ 12:27 ቀጥሎ) ጸሐፊው በነህምያ 11 እና 12 ላይ የዘር ሃረግ ተንትኖ ከጨረሰ በኋላ ወደ ከተማዋ ቅጥር ግንብ ምርቃት በዓል ወቅት ይሸጋገራል። ለእግዚአብሔር ነገሮችን መርቆ መስጠት በህዝቡ ዘንድ የተለመደ ነበር፤ ቤተ መቅደሱን፣ የከተማውን ቅጥር፣ ብሎም ቤቶችንና ህንጻዎችን። እንደዚህ አይነት ምርቃቶች በጥንቃቄ ታስቦባቸው ተዘጋጅተው በዝማሬ፣ በሙዚቃ፣ በፌሽታ፣ በመስዋዕት፣ በውዳሴ፣ በደስታና በህዝቡ መንፃት የታጀቡ ናቸው። ዳዊት በምርቃት ጊዜ መስዋዕት የማቅረብን ልምምድ መሰረተ፤ ከዚያም በመቀጠልከሰለሞን የቃል-ኪዳኑን ታቦት ወደ መቅደሱ በማምጣት(1ኛ ነገ 8:5)ይጀምርና የእስራኤል ነገስታት ሁሉ የእርሱን ምሳሌ ተከተሉ። በዚህ ሳምንት በዚያን ጊዜ እንዴት እግዚአብሔርን እንዳመለኩ እናይና፤ ይህንኑ አምላክ የምናመልክእኛ ደግሞ እንዴት ለራሳችን ተግባራዊ ማድረግ እንደምንችል እንመለከታለን። ለሕዳር 27 ሰንበት ለመዘጋጀት ያንብቡት።

ህዳር 21
Dec 01

የእግዚአብሔርን ዝማሬዎች መዘመር


ነህምያ 12:27-29ን ያንብቡ። አምልኮና ውዳሴያቸው እንዴት እንደነበር የሚገልጹትን የተወሰኑ ቁልፍ ቃላት አስተውሉ። እናንተ እንዴት ትገልጿቸዋላችሁ?የእስራኤል ሕዝብ ከሌዊ ወገን የተወሰኑትን ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ ዘማሪያንና ሙዚቀኞችን አድርጎ ለይቶ ነበር። የቤተመቅደሱ አምልኮ ባማረና በሰለጠነ አግባብ እንዲፈጸም እግዚአብሔር እራሱ ስራዓቱን ተቆጣጠረ እናም ለአገልግሎቱ አካሄድ ትዕዛዛትን ሰጠ።

ንጉስ ዳዊት ይህን ልምምድ ከዚህ በፊት ከተደረገው ስርዓት ይልቅ ግልጽ በሆነና በሚያስደንቅ መልኩ ነበር ያቀናጀው።ስለዚህም እራሱ ዳዊት በቤተ-መቅደሱ ውስጥ የሚደረገውን አምልኮ እንዲመሩ ሃላፊነት የሰጣቸው የአሳፍ ትውልድ አሁንም “በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን…”(ነህ 11:22) መካከል ተሰይመው ነበር።

1ኛ ዜና 25:6-8ን ተመልከቱ። ይህ ክፍል ሙዚቃ ምን ያህል ለአምልኮ እና ለዝማሬያቸው “የእግዚአብሔር ዝማሬዎች” አስፈላጊና ማዕከላዊ እንደነበር እንዴት ያስተምረናል?ዘማሪያኑ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የተለዩት ሌዋውያን ነበሩ። እናም ለቤተመቅደሱ አገልግሎት መዝሙር ማዘጋጀት ስራቸው ነበር። በንጉስ ዳዊት ዘመነ መንግስት እራሱ የሚቆጣጠረው ሙሉ ለሙሉ የተሟላ የሙዚቃ አካዳሚ ተቀናጅቶ ነበር። በፈረቃ ለቤተ መቅደሱ ሙዚቃ በማቅረብ የሚሰሩ ተማሪዎችና አስተማሪዎች፤ ልጆችና ወጣቶችም ነበሩት። አንዳንዶች የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾች፣ ሌሎች ዘማሪዎች፣ ሌሎች ደግሞ የሙዚቃ መሳሪያውንና ለአገልግሎቶቹ የሚለበሱትን አልባሳት ይቆጣጠሩ ነበር። እንደዚህ የተቀናጀ ድርጅት አላማው ምን ነበር? ተሰጥዖንና በአምልኮ የመላቅን አላማ ለማሳደግ ያገለግል ነበር። ልህቀት ሁልጊዜም የአምልኮ አላማ መሆን አለበት። ሰዎች በመንፈስ መነቃቃት ይችሉ ዘንድ ወዳሴዎች ከልብ መፍለቅ እና ግሩም በሆነ ሁኔታ መገለጽ አለባቸው። የቤተ-መቅደሱን የአምልኮ ስነስርዓት እንዲመሩ የሚመረጡት ሙዚቀኞችና ዘማሪያን በጥንቃቄ የተመረጡ ናቸው ተብሎም ሊገመት ይችላል።

በሙዚቃ የማምለክን ደስታ የተለማመዱባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው? ይህስ ለእርስዎ በምን መልኩ አስፈላጊ ነው?

ህዳር 22
Dec 02

መንፃት


መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቅጥሩ መመረቅ ቀጥሎም ስለ መዘምራኑ መሰባሰብ ከተናገረ በኋላ፤ ቀጣዩ ጥቅስ ነህምያ 12:30 ስለ መንፃት ይናገራል። “ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ።”

“ነፃ” ለሚለው የዕብራውያኑ ስርወቃል፤ “thr” ማለት ንጹህ መሆንና መጽዳት ማለት ነው፤ በእግዚአብሔር ፊት በሞራል ንጹህ መሆንና ጥርት ማለትን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች በብሉይ ኪዳን ጥቅም ላይ ውሏል።

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። “(1 ዮሐ. 1:7-9)። ይህ ጥቅስ ስለ 1)ሰው ተፈጥሮ፣ 2) የእግዚአብሔር ይቅር ባይነት እና 3) እግዚአብሔር በህይወታችን ውስጥ ስላለው ሀይል ምን ያስተምረናል?ቤተ መቅደሱና በውስጡ ያለው አገልግሎት ለጥንታዊ እስራኤል አስፈላጊ ሃይማኖታዊ ክፍል ነበር። ነገር ግን ቤተ መቅደሱና በውስጡ ያሉት አገልግሎቶች የፍጻሜው መገለጫዎች ነበሩ እንጂ እራሳቸው ፍጻሜ አልነበሩም። እናም ፤ በእርግጥም የዚህ ፍጻሜ አላማ ደግሞ ህዝቡን ከባለ ቃልኪዳኑ አምላካቸው ጋር ያላቸውን የደህንነት ግንኙነት እንዲያስተካክሉ የሚመራና ወደ ጌታችን የሱስ ክርስቶስ እያመላከተ የእርሱን የማንጻት ሃይል በሕይወታቸው እንዲያሳውቅ ነበር። እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር ብሎም ጌታችን ከምን እንዳዳነን ማወቅ ነው እግዚአብሔርን ወደ መውደድ እና እርሱን ወደ ማምለክ የሚመራን። የጥንት እስራኤላውያን እግዚአብሔር ድሮ ያደረገላቸውን ነገር ደግመው ደጋግመው የሚቆጥሩበት አንደኛው ምክንያት ይህ ነው። እርሱም የእግዚአብሔርን መልካምነትና ፍቅር እንዲያውቁ በማገዝ የአምልኮ ልምዳቸውን የሚያቃጣጥለው ደስታና ምስጋናቸው ማዕከል ነበር።

እኛም ዛሬ ለኃጢአት ይቅርታ ማግኘታችንን ማወቃችንና ማድነቃችን ምስጋናን ለእግዚአብሔር እንድንሰጥና ዘላቂ ደስታን ሊያመጣልን ይገባል። ከዚያ እግዚአብሔርን ማክበር እና ለግሩም ባህሪው ያለንን አድናቆት መግለጽ ቀላል ይሆናል። ክርስቶስን በመስቀል ከማየትና እኛ ራሳችን ቅጣትን እንዳንቀበል ሲል ሃጢአታችንን ከመሸከም የበለጠ የእግዚአብሔርን ባህሪ ሚገልጽ ምን አለ? የቀድሞ ሃጥያታችሁ ወይንም የአሁን ማንነታችሁ ምንም ይሁን ምን፤ በመስቀሉ ስር እናንተም ሁላችሁ ሙሉ ለሙሉ ይቅርታን የመቀበል መብት አላችሁ። ክርስቶስ የሚያቀርብላችሁን ይቅርታ ለምን አሁኑኑ አትቀበሉም?

ህዳር 23
Dec 03

ሁለት ታላላቅ የምስጋና መዘምራን


ነህምያ 12፡ 31-42ን ያንብቡ። ለምን ነበር ሙዚቃ የዚህ ክብረ በዓል ዋና ክፍል የሆነው?በነህምያ ጊዜ በእየሩሳሌም ዙሪያ በሙዚቃ መሳሪያ ታጅበው የሚዘምሩ ሁለት የምስጋና መዘምራንን መመስረት የአምልኮው ስነስርዓት አንዱ አካል ነበር። በከተማው ቅጥር ዙሪያ በተለያየ አቅጣጫ ለመሄድ ከአንድ ቦታ ጀምረው ለሁለት ይከፈላሉ። አንድ ቡድን ፈት ለፊት በሚሆነው በዕዝራ ይመራ ነበር፤ ለሌላው ቡድን ደግሞ ከኋላ ባለው በነህምያ። ሁለቱ የመዘምራን ቡድን በመጨረሻ የሸለቆ በር ጋ ይገናኙና ከዚያ ወደ ቤተ-መቅደሱ ያመራሉ። መለከት የሚነፉት ካህናትም ለእያንዳንዱ ስነስርዓት ምስጋና ይሰጣሉ። ቤተመቅደስ በገቡ ሰዓት ሁለቱም የመዘምራን ቡድን ፊት ለፊት ለፊት ለፊት ይቆማሉ። እጅጉን የተቀናጀ የሰልፍና የአምልኮ አገልግሎት ነበር።

ሙዚቃ ለምን የውዳሴ እና አምልኮው ዋና ክፍል እንደሆነ ለመመለስ ከቤተመቅደሱ አኳያ ያለውን ትርጓሜ ማየት አለብን። በቤተ መቅደስ ውስጥ ያለ ሙዚቃ፤ ሰዎች መጥተው በትልቅ አዳራሽ ውስጥ እንደተዘጋጀ 4ተኛው የቤቶቨን ጣዕመ ዜማ የሚደሰቱበት አይደለም። ነገር ግን ሙዚቀኞቹ በዘመሩና ሙዚቃ መሳሪያ በተጫወቱ ቁጥር ህዝቡ በጸሎት ይሰግድ ነበር። የአምልኳቸው ክፍል ነበር።

የቤተ መቅደሱ ስነስርዓትና የአምልኮው ሂደት በመስዋዕት ላይ ያተኮረ ስለሆነ ብዙም የሚስብ አልነበረም። የንጹህ እንስሳትን አንገት ከመቅላት የተሻለ ምን ያደርጉ ነበር? እንደዚህ አይነት ሙዚቃ መጫወታቸው በብዙ መልኩ የህዝቡን ልብ ወደ ሰማይ ከማነሳሳት ባለፈ አጠቃላይ የአምልኮውን ስነ ስርዓት የተሻለ መልካም መዓዛ ሰጥቶታል። እስኪ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሙዚቃ የአምልኮ ዋነኛ አካል የነበረበትን ሁኔታ ዘልቀው ይመልከቱ። በተለይ በዘፀ 15:1፤ 2 ዜና 20:21, 22፤ እና ራዕ 15:2-4 ላይ ያለውን ይዘት ይመልከቱ።በሰማይም በምድርም ሙዚቃ የአምልኮ ልምምድ አካል ነው። ከላይ ባሉት ጥቅሶች ውስጥ ልብ ይበሉ፤ ዝማሬው እግዚአብሔር ለሕዝቡ ካደረገው ነገር አንጻር ብቻ ነበር ፤ “በአውሬው ላይ” ድል እንዲቀዳጁ ማድረጉን ጨምሮ (ካልሆነ ሌላ በምን መልኩ ያንን ድል ይቀዳጃሉ?) ለደህንነት ተግባሩ እግዚአብሔርን የሚያወድሱበት ነበር።

በዝማሬ ለማወደስ መልካም ምክንያት የሆኑ አንዳንድ እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ነገሮችን ጥቀሱ?

ህዳር 24
Dec 04

መስዋዕቶች፤ እንደ አምልኮ አካል


ነህ 12:43ን ያንብቡ። ልክ እንደ አምልኮ ስነስርዓት አካል ፤ ታላላቅ መስዋዕቶችን መሰዋት ምን የተለየ ነገር ነበረው?በቤተ መቅደሱ ጊዜ መስዋዕቶች ማቅረብ እጅግ አስፈላጊ የአምልኮ አካል ነበር። ለይቅርታ ቃልኪዳን ወይንም ለእግዚአብሔር ያላቸውን ክብርና ህብረት ለመግለጽ በርከት ያሉ የተለያዩ መስዋዕቶች ያደርጉ ነበር። ለመዕመኑ የእግዚአብሔርን እውነትና ማንነት ስለሚያስታውስ ፤መስዋዕት፤ የአምልኮን አላማ ማሳወቂያ መሰረተ ሃሳብ የያዘ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔር በግ ስለሆነ እራሱን ለእነርሱ የሚሰዋውን የቃልኪዳኑን በግ መሲሁን ያመላክት ነበር።

ዮሐንስ 1:29፡36፤ 1ቆሮንቶስ 5:7፤ እና ዮሐንስ ራዕይ 5:6፤ 12፤ 13ን ያንብቡ። መስዋዕቶች በስተመጨረሻ ወዴት እንደሚያመላክቱ ምን ይነግሩናል? የቀድሞ እስራኤል ውስጡ ከሁሉ የላቀ እውነት በያዘ በሞተ የቤት እንሰሳ የሚደሰቱ ከሆነ እኛ ከእነርሱ በላቀ የምንደሰትበት ምን የበለጠ ምክንያት አለን?በነህምያ 12:43 ብቻ ስንት ጊዜ ደስታ እና ደስ የመሰኘት ሃሳቦች እንዳሉ ያስተውሉ። ይህ ደስታና ውዳሴም የሞላበት የአምልኮ አገልግሎታቸው ምናልባትም እግዚአብሔርን ከመፍራት እና ከማክበር (ሆነም ቀረ ለሃጢአታቸው እንሰሳን መስዋዕት ማቅረባቸው ክቡር ተግባር ነበር) የተነሳ ከተለማመዱት ተግባራት መሃከል ነበር።

በእግዚአብሔር ፊት ስንቀርብ በፍርሃትና በክብር ብሎም በውዳሴ መሆን አለበት። መዝ 95 ትክክለኛ የክብር ተግባር እንድንዘምር በማመላከት፤ ደስ እንዲለን እና ለመድኃኒታችን እልል እንድንል (95:1) እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት እንድንሰግድና እንድንንበረከክ (መዝ 95:6) ይገልጽልናል። በደስታና በአምልኮት መካከል ያለው ሚዛናዊነት ጋር መድረስ፤ ለክብር፣ ለውዳሴ እና ፈጣሪያችንን ለማምለክ አስፈላጊ ነው።

የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ (ዮሐ፡!፡1-3ን ተመልከቱ) የሆነው በመስቀል ላይ መስቀሉን፣ ለፈጠረው ፍጥረት ሐጢያት መሞቱን ስናስብ መጀመሪያ የሚሰማን ስሜት ምንድን ነው? በመስቀሉ ልምምዳችን ደስታስ ምን ሚና መጫወት ይኖርበታል፣ ይችላልስ?

ህዳር 25
Dec 05

ካህናትና ሌዋውያን እንደ አምልኮ አካል


ነህ 12:44-47ን ያንብቡ። ይሁዳ ባገለገሉት ካህናትና ሌዋውያን ምክንያት ለምን ተደሰተ። ለምን ነበር እነርሱ አስፈላጊ የነበሩት?(ሌዋውያን የነበሩት) ካህናት ስራ ምንን ያመላክታል? ዕብ. 9:1-11. ይመልከቱ።ልክ እንደ መስቀል ሞቱ ሁሉ በላይ በሰማይ ቤተ መቅደስ ክርስቶስ ስለሰው የሚያደርገው የማማለድ ስራ ለደህንነት እቅድ እጅግ አስፈላጊ ነው። በሞቱ ምክንያት ከትንሳኤው በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ የሚጨርሰውን ያንን ስራ ጀመረ። በእምነት ከእርሱ ሽፋን ስር መግባት አለብን “በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ።” ዕብ. 6:20 ኤ.ጂ. ኋይት፣ ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 489።

በእርግጥ ምንም እንኳን በዚያን ዘመን የነበሩ ሰዎች እኛ አሁን ያለን ብርሃን ባይኖራቸው፤ ቤተ መቅደሱን ብቻ የሚያገለግሉትን የሌዋውያኑን ስራ ግን በበቂ ሁኔታ አስተውለው ነበር። የእግዚአብሔር ስራ በእነርሱ በኩል በመሰራቱ ደስተኞች ነበሩ።

የአገሩ ህዝብ በጠቅላላ የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ፣ በመጸለይ፣ በማምለክ፣ ራሳቸውን ለርሱ ደጋግመው በመስጠት ጊዜን ያሳልፉ ነበር። ከዚህ ሁሉ መካከል የቤተመቅደሱ አገልግሎት እንደተዘነጋና መታደስ እንዳለበት አስተዋሉ። አሁን እነዚህ በድጋሚ ሲቋቋሙ ሌዋውያኑ ስለ እነርሱ ሊሰሩ የሚችሉትን ስራ በማሰብ ተደሰቱ። በቤተመቅደሱ ያሉ አገልግሎቶች እግዚአብሔር ለአምልኮ ያለው ንድፍ አካል እንደሆነ በማሳየት ህዝቡን አስደነቃቸው። ነገር ግን አገልጋዮች፣ የቃሉ አስተማሪዎች እና ሙዚቀኞች ብዙ ጊዜ በትክክል አይስተዋሉም። በነህምያ ጊዜ እንኳ የሌዋውያን እገዛ አንዳንዴ ጠንካራ አንዳንዴ በጣም ደካማ ነበር። ሰዎች አስራታቸውንና መብዓቸውን መስጠት ስላቆሙ ብዙ ጊዜ ሌዋውያኑ ቤተሰባቸውን ለማገዝ ወደተለያየ ስራ መሰማራት ነበረባቸው። በአለም ዙሪያ ያለ አስራትና ስጦታ የተቀናጀ ቤተክርስቲያን የለም። ሚኒስትሪዎቻችን እንዲቀጥሉ ከፈለግን ባለን ገንዘብ እንዲሁም በቃል ማበረታቻዎች አገልጋዮቻችንን ለማገዝ መትጋት ይኖርብናል።ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢሆን ፍጹም ላትሆን ትችላለች፤ ነገር ግን ይህ ለቤተ ክርስቲያን የምንሰጠውን ሊያሳንስብን አይገባም፤ ምክንያቱም በዓለም ዙሪያ የሚሰራው ስራ ይቀጥል ዘንድ።

ህዳር 26
Dec 06


ተጨማሪ ሀሳብ


የኤለን ጂ. ኋይት “ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ መንገድ“ ከሚለው መጽሐፍ ወደ ክርስቶስ ማደግ የሚለውን ክፍል በእንግሊዝኛው ገጽ 6775ን ያንብቡ። “ለዘለዓለም ዓለም የክርስቶስ መስቀል የደህንነት ሳይንስና ዝማሬ ይሆናል። በክርስቶስ ክብርን ተቀብለው የተሰቀለውን ክርስቶስን ያመሰግናሉ። በሃይሉ ሰማያትንና የማይቆጠረውን ሰፊውን የጠፍር ግዛት የመሰረተና ያቆመ፣የእግዚአብሔር ተወዳጅ ፣ የሰማዩ ክቡር፣ ያ ኪሩብ የሚያበራ ኮከብ የወደቀውን ለማንሳት ራሱን ዝቅ ያደረገ፣ የሃጢአትን ጸጸትና ሃፍረት የተሸከመ እና ከአባቱ ፊት የሰወረ፣ የሚጠፋው አለም ጩኽት ልቡን እስኪሰብርና ህይወቱን በቀራንዮ መስቀል እስኪሰዋ ያደረገ ፤እርሱ፤ መቼም የሚረሳ አይደለም። ለሰው ልጅ ካለው ፍቅር የተነሳ የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ፣ የፍጻሜዎች ሁሉ የበላይ፣ ክብሩን ሁሉ ወደጎን ትቶ መምጣቱ የዩኒቨርስን አድናቆትና ክብር ያልፍ ይሆን። የዳኑት ህዝቦች አዳኛቸውን ሲመለከቱ እነሆ በፊቱ ዘላለማዊ ክብር ያለው አባቱ ሲያበራ፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም የሆነውን ዙፋኑን ሲያከብሩ፣ ንግስናውም ፍጻሜ እንደሌለው ሲያውቁ፣ ታላቅ ደስታና ሃሴት በሞላው ዝማሬ ይሞላሉ “ብቁ ብቁ ነው የተሰዋው በግ እናም ለእግዚአብሔር አድኖናል በከበረው በራሱ ደም”” ኤለን ጂ.ኋይት ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 651,652


የመወያያ ጥያቄዎች
1.በሰንበት ት/ት ክፍላችሁ በደስታና በአምልኮ መካከል ትክክክለኛውን ሚዛን እንዴት እንደሚገኝ ተነጋገሩበት። ወይንም በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ተነጋገሩ፡ አምልኮና ደስታ የተለያዩ ነገሮች ናቸው?
2.በምረቃ ስነስርዓቱ እስራኤላውያን የእየሩሳሌምን ከተማ ቅጥር በመለኮታዊው ጥበቃ ስር አደረጉ፤ እናም ቅጥር እግዚአብሔር ካልጠበቀው ዋጋ እንደሌለው አረጋገጡ። ሰለሞን በሚገባ ገልጾታል “እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።” (መዝ. 127:1) ይህ ታድያ ለወደፊቱ ለጌታ ስለምናደርጋቸውን ጥረቶች ምን ይነግረናል?
3.በእርስዎ ቤተ ክርስትያን በአምልኮ ውስጥ የሙዚቃ ሚና ምንድን ነው?
4.መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ ነው፡ በሰማይ ቤተ መቅደስ ክርስቶስ ሊቀካህናችን ነው። በዚያ ለእኛ በትክክል የሚያደርግልን ምንድን ነው? ክርስቶስ በሰማይ ለእኛ እያደረገ ስላለው ስራ በምድር ቤተመቅደስ ውስጥ የሚያገልግሉ አገልጋዮች የሚያስተምሩን ነገር ምንድን ነው?